Song Lyrics

ምሳሌዬ

Hana Tekle
Agizegn
ምሳሌዬ አንተው ነህ በምግባርህ የማውቕ ንግግርህ ከሩቅ ይጠራል ጨዋነትን ተላብሰሃል ከውስጤ ገብተህ ቀርተሃል ማን ቢፈለግ ይተካሃል ጥበብ ፍቅርም በአንተ ይለካል አዋቂነት ከአንተ ይቀዳል አዝ:- አስተዋይ ወዳጄ ብልህ ብትገባኝ ነው ባውቅህ ጠቢብ ብዬ ብጠራህ ቃል አጥቼ ለስምህ ጻድቅ ፍፁም ነህ (4x) አለቅነት በአንተ ያምራል አስተዳደር በአንተ ይሰላል መታገስህ ሁሉን ያልፋል መቼ ፍርድህ ቀድሞ ያውቃል የሊቅ ጥጉ መደምደሚያ የትሁት ልብ ማሳረጊያ ፍትህ ሚዛኑ በአንተ ከወጣ ዳኝነቱም ከአንተ ይምጣ አዝ:- አስተዋይ ወዳጄ ብልህ ብትገባኝ ነው ባውቅህ ጠቢብ ብዬ ብጠራህ ቃል አጥቼ ለስምህ ጻድቅ ፍፁም ነህ (4x) የሁሉን ከፍታ ይዘሃል ወርደህም ማዳን ሆነኃል ከፍም ብለህ ዝቅም ብለህ ፍፁም ጌታ አንድ አንተ ነህ ሁሉን በእኩል የምታየው ምስኪኑንም የማትንቀው የደግነት መገለጫ የሁሉ አባት አንተ ብቻ ውዴ ውበትህ ማንነትህ ደም ግባትህን አይቼው አይቼው አልችልም ልገልጽህ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection