Song Lyrics

ወንጌል ሰላም

Hana Tekle
Agizegn
ይነገር ለዓለም ቅዱሱ መጽሃፍ ከዳር ዳር ሰማሁ እውነቱ አይታለፍ ዘር ቀለም ላይለየው ለሁሉም ተፈቅዷል ለወደዱት ሁሉ ሰላምን ይሰጣል አዝ:- ወንጌል መሪ ወንጌል ሰላም ለሰው ልጆች ይሁን መዳን ለህዝባችን ይሁን መዳን (2x) የታሰሩ ይፈታሉ የታመሙት ይድናሉ ይፈታሉ ይድናሉ ፈውስ ነው ወንጌሉ (ኡዎዉዎዎ) ፈውስ ነው ወንጌሉ ፈውስ ነው ወንጌሉ (2x) ሊታረም የማይችል ፍፁም እውነት አለው ሊሽረው የቆመ የትኛው ጠቢብ ነው የጠቢባን ጠቢብ ይህን ከገለጸው የደህንነት መንገድ ኢየሱስ ብቻ ነው አዝ:- ወንጌል መሪ ወንጌል ሰላም ለሰው ልጆች ይሁን መዳን ለህዝባችን ይሁን መዳን (2x) የታሰሩ ይፈታሉ የታመሙት ይድናሉ ይፈታሉ ይድናሉ ፈውስ ነው ወንጌሉ (ኡዎዉዎዎ) ፈውስ ነው ወንጌሉ ፈውስ ነው ወንጌሉ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection