አግዘኝ ደግፈኝ ብዬ ነበረ የእኔ ጌታ ሰማኸኝ ስለቴም ሰመረ ብዬ እልሃለው እንደገና በአዲስ ዝማሬ በአዲስ ዜማ የአየሁትን በዓይኔ አይቻለሁ እጅህን በብዙ አይቻለሁ ምሥጋናዬ በፊትህ ያርግልኝ አምልኮዬ በፊትህ ይፍሰስልኝ ዝማሬ በፊትህ ሞገስ ያግኝልኝ አንተ አይደለህም ወይ ረዳቴ በጭንቅ ዘመን እረፍቴ በማያምር ቀን ወበት ድምቀቴ የደስታዬ ድምጽ ጩኸቴ (2x) የለኝም ሌላ እኔ የምለዉ ይሄ ነው ብዬ እንኳን የማነሳው ከሰው የድስታዬ ቀኑ ባለቤት ብቻህን ታይበት ይህን ነው የምለው ተመሥገን ተመሥገን (8x) አዘኑ ክፉ ያዩልኝ ቀኖቼ እንባን የሻቱ ለዓይኖቼ ቀኔን አዘኸው ከላይ ከሠማይ ጠገብኩ በደስታ ሳቅ ሲሳይ (2x) የለኝም ሌላ እኔ የምለዉ ይሄ ነው ብዬ እንኳን የማነሳው ከሰው የድስታዬ ቀኑ ባለቤት ብቻህን ታይበት ይህን ነው የምለው ተመሥገን ተመሥገን (8x) ይገባሃል ተመሥገን (4x) ተመሥገን (4x)