አዝ:- አንተን ጠርቶ ማን አፈረ ተማምኖብህ ማን ከሰረ የተዘጋን ትከፍታለህ የታሰረን ትፈታለህ የታመመን ታድናለህ የሞተውን ታስነሳለህ ስልጣን የአንተ ጌታዬ ሆት ስልጣን የአንተ ስልጣን የአንተ የኔ ጌታ ስልጣን የአንተ ስልጣን የአንተ ጌታዬ ሆይ ስልጣን የአንተ የፈጠረን በረሃ በሌለበት ውሃ በምድረበዳ ለተጐዳ ዘመድ ለሆነው ባዳ እንደ ማለዳ አምቆ ሚስጥሩን በልቡ ጓዳ እንባውን የጻፈ በጸሎት ሰሌዳ ለቆዘመው ብቸኛ ለሌለው ጓደኛ ሃሩር ላከሰለው መንገደኛ የሚቀምሰው ላጣ ረሃብተኛ በሀገር በምድሩ ስደተኛ በወገኑ መሃል መጻተኛ ድሃ ችግረኛ የሆነም እንደኛ ለሚሻህ ቅን ፈራጅ ዳኛ ከቤቱ ሳይወጣ መናን የሚሻ ለነፍሱ አጽናኝ ደራሽ አዛኝ ለስብራቱ ጠጋኝ በሩን ዘግቶ ለሚያለቅሰው ነገር ከብዶት ሆድ ለባሰው አጥቶ እንባውን የሚያብሰው ረድኤት የሚሆነው ከሰው ማነው የሚደርሰው ጌታ ነው ኢየሱስ ጌታ ነው (5x) ለብቸና ተጓዥ መንገደኛ የፍቅር አምላክ እውነተኛ ፍቅር ማነው እግዚአብሔር ነው ፍቅር ማነው ኢየሱስ ነው ኃጢአት አሸፍቶት ጫካ የገባውን ጸጋውን ተገፎ የተራቆተውን የበደሉን ብዛት መሸከም ላቃተው ነገር ግራ ገብቶት ለሚወተውተው የእዬዬ ኑሮ የለቅሶ ሸለቆ የጨከነ ውጋት ሃዘናትን ዘልቆ በጦርነት ሜዳ ፍልሚያ መሃል ወድቆ ፈገግታ ከፊቱ ከቤቱ ሳቅ ርቆ እንባው ካይኑ ደርቆ ሃዘን ኑሮ ሲከፋ ረዳት ወገን ሲጠፋ ወጀብ አውሎ ሲከፋ የመከራ ጉም ሲያካፋ መስቀሉ ስር ሲደፋ ጌታ ኢየሱስ ደርሶ እንባውን አብሶ የጽድቅ ልብስ አልብሶ አሮጌን አድሶ በፍቅሩ እጁ ዳሶ በደሌን ደምስሶ አጥቦና ቀድሶ ፈውሶ በክብር ያቆማል ጥያቄን መልሶ ጌታ ነው ኢየሱስ ጌታ ነው (5x) አዝ:- አንተን ጠርቶ ማን አፈረ ተማምኖብህ ማን ከሰረ የተዘጋን ትከፍታለህ የታሰረን ትፈታለህ የታመመን ታድናለህ የሞተውን ታስነሳለህ ስልጣን የአንተ ጌታዬ ሆት ስልጣን የአንተ ስልጣን የአንተ የኔ ጌታ ስልጣን የአንተ ስልጣን የአንተ ጌታዬ ሆይ ስልጣን የአንተ