Song Lyrics

ፈገግታ

Dawit Wolde
Mezmur 91
የትም ባክኜ እንዳልጠፋ እንደሌላቸው ተስፋ አምላኬ ጐዳናዬን መንገዴን አሰፋ ደረቁ ምድረ በዳ በውሃ እንዲረካ በምንጩ ደስ አሰኘኝ ጨለማዬ ፈካ የመርገም ጨርቄን ቀደደዉ መተላለፌን አራቀዉ እግሬን አጸና በከፍታ ወዶ አዳነኝ የኔ ጌታ በተከበበች ከተማ አጽናኝ ድምጽ እያሰማ በአስደናቂ ምሕረቱ አኖረኝ በቤቱ ሲጠብቀኝ መች ሰንፎ አቤት ስንቱን አሳልፎ ከቶ አለ ለታምራቱ ከልቤ ተጽፎ በባዕድ ምድር ጓደኛዬ (ጓደኛዬ) ሳዝን መጽናኛዬ (መጽናኛዬ) ታሪኬን ሞላው በመዝገቡ ከፍ ይበልልኝ ታላቅ ስሙ አፌን ሞላው በሳቅ ዝማሬ ተረጋጋ ዙሪያ ሰፈሬ ስለ ሥሙ ያደረገው ምስጋናው እጅግ ብዙ ነው (2x) ጌታ ፊት አይቶ አያዳላ አምላኬ የምስኪን ጥላ ተማምነው ለጠበቁት ይደርሳል ሲጠሩት እኔም እርሱን ታምኜ በእድሜ በሕይወት ዘመኔ አልቀረሁም በከንቱ አለሁኝ በቤቱ አባ አባት ብዬ ተጣርቼ (ሥሙን ጠርቼ) በእምባ በጸሎት ደጅ ጠንቼ ምልጃዬን ሰምቶ (ምልጃዬን ሰምቶ) አልጨከነም (ምሕረቱን ከእኔ) ምሕረቱን ከእኔ አላራቀም አፌን ሞላው በሳቅ ዝማሬ ተረጋጋ ዙሪያ ሰፈሬ ስለ ሥሙ ያደረገው ምስጋናው እጅግ ብዙ ነው (7x) ምስጋናው እጅግ ብዙ ነው (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection