አዝ፦ የሰማይ የምድር የፍጥረት ንጉሥ ለእኔ ይህ ክብር ነው አንተን ማወደስ የቁጣ ልጅ ሳለሁ ቀድሞ ከፍጥረቴ ሳስብ ይደንቀኛል በስምህ መጠራቴ ተደምስሶ ኃጢአቴ የዕዳ ጽህፈቴ በአንተ በመታየቴ ስምህን አነግሣለሁ ማዳንህን ስላየሁ መዝሙር እዘምራለሁ ፍቅርህን ስላየሁ እጥፍ አሰግዳለሁ ለክቡርነትህ አምልኮ አቀርባለሁ ለአምላክነትህ አዝ፦ የሰማይ የምድር የፍጥረት ንጉሥ ለእኔ ይሄ ክብር ነው አንተን ማወደስ አንተን ማሞገስ ዝናህን ሰምቼ በዓይኖቼ አይቼ ለክብርህ ሰገድኩኝ ጌታ አምላኬ አልኩህ ቤቱን የሞሉትን ፈሪሳውያንን ሳትፈራ የናርዶስንሽቶ በእግሮቹ ሥር ሰብራ እንባዋን አፍስሳ ክብሯን ሁሉ ጥላ እንዳመለከችው የነፍሷን ከለላ እኔም ከሕይወቴ ሳልቆጥብ ከአንጀቴ ዜማ መስዋዕቴ አዝ፦ የሰማይ የምድር የፍጥረት ንጉሥ ለእኔ ይሄ ክብር ነው አንተን ማወደስ አንተን ማሞገስ ዝናህን ሰምቼ በዓይኖቼ አይቼ ለክብርህ ሰገድኩኝ ጌታ አምላኬ አልኩህ ገና በሩቅ ሳለሁ በስሜ ያወቅከኝ የርስትህ ተካፋይ ወራሽ ያደረከኝ ለሰው አስቸጋሪ ድካም ጉድለቴን ችለህ ስወድቅ ስነሳ አይዞህ ልጄ ብለህ በክንድህ ደግፈህ በፍቅር እጅህ ዳሰህ አቆምቀኝ ሰው አርገህ ሥምህን አነግሳለሁ ማዳንን ስላየሁ መዝሙር እዘምራለሁ ፍቅርህን ስላየሁ እጥፍ አሰግዳለሁ ለክቡርነትህ አምልኮ አቀርባለሁ ለአምላክነትህ አዝ፦ የሰማይ የምድር የፍጥረት ንጉሥ ለእኔ ይሄ ክብር ነው አንተን ማወደስ አንተን ማሞገስ ዝናህን ሰምቼ በዓይኖቼ አይቼ ለክብርህ ሰገድኩኝ ጌታ አምላኬ አልኩህ ጌታ አምላኬ አልኩህ (4x)