ሥምህን ሳስጠራ በዝማሬ በቤትህ ስኖር እስከዛሬ አይጠገብም ከማር ይጥማል ሥምህ ከሥሞች ሁሉ ይልቃል ያንተን ውለታ ነፍሴ ተረድታ ታከብርሃለች ጠዋትና ማታ ታከብርሃለች ቀንና ማታ ቀናት አለፉ እንደ ጥላ አምና ካቻምና ቀረ ከኋላ ባሳለፍኳቸውዘመኞቼ አፍሬ አላወቅም አንተን ጠርቼ የጸና ክንድ ነው መሸሸጊያ ጌታዬ ስምህ መጠለያ ካለም ጥፋት ማምለጫ ጥላ አዝ፦ ኢየሱስ ጌታዬ አምላኬ እኔ ከቶ አልጠግብም ሥምህን ጠርቼ ብዙ ምስጋናህን ዘምሬ መስክሬ አባ አባት ብሎ ማነው ያፈረ አንተን ተማምኖ ከስሮ የቀረ ጻድቅ ተርቦ ዘሩ ሲለምን በታሪክ የለም አልሰማንም ለኔስ ማትረፍ ነው ቤትህ መኖሬ ያንተን ምስጋና መዘመሬ ቅዱስ ሥምህን መመስከሬ አዝ፦ ኢየሱስ ጌታዬ አምላኬ እኔ ከቶ አልጠግብም ሥምህን ጠርቼ ብዙ ምስጋናህን ዘምሬ መስክሬ (2x) ኢየሱስ ሥምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው አጥንትን ሁሉ ዘልቆ እንደሚገባ ነፍስንም እንደሚያረሰርስ ቁስልንም እንደሚፈውስ መልካም መዓዛ ያለው ዘይት ነው ለክቡር ሥምህ እዘምራለሁ ኢየሱስ (ኢየሱስ) ጌታዬ (ጌታዬ) መድህኔ (መድህኔ) አመልክሃለሁ