Song Lyrics

እኔ የማመልከው

Dawit Wolde
Mezmur 91
የጌታን ውለታ በምን እመልሳለሁ ዘላለም ላመልከው ቃል ገብቻለሁ የአምላኬን ውለታ በምን እመልሳለሁ ዘላለም ላመልከው ቃል ገብቻለሁ ችግረኛን የሚታደግ የቆሰለን የሚፈውስ ለታመነው ፈጥኖ የሚደርስ ሥሙ ጌታ ኢየሱስ ማዕበሉን አሳለፈኝ ወጀቡንም አሻገረን እጄን ይዞ እየመራ እዚህ አደረሰኝ አዝ:- እኔ የማመልከው ጌታዬ አባት ወንድም ጓደኛዬ የጸና ስሙ መሸሸግያዬ በፍቅሩ ተማርኬያለሁ ፍቅጄ አመልከዋለሁ ለዘላለም ለእርሱ እገዛለሁ (2x) ያን ፈተና የገነነ እንደተራራ የሆነ የአምላኬን ስም ስጠራበት እንደ ጉም ተነነ የባሕሩም ወጀብ ከብዶ ነፍሴን በሌት አስጨንቋት ግን ጌታዬ ምን ተስኖት ተረማመደበት አዝ:- እኔ የማመልከው ጌታዬ አባት ወንድም ጓደኛዬ የጸና ስሙ መሸሸግያዬ በፍቅሩ ተማርኬያለሁ ፈቅጄ አመልከዋለሁ ለዘላለም ለእርሱ እገዛለሁ (2x) የጌታን ውለታ በምን እመልሳለሁ ዘላለም ላመልከው ቃል ገብቻለሁ የአምላኬን ውለታ በምን እመልሳለሁ ዘላለም ላመልከው ቃል ገብቻለሁ እግዚአብሔር እረኛዬ የማይተኛ ጠባቂዬ በክፉ ቀን ማምለጫዬ ሥሙ መከታዬ ይመራኛል አምነዋለሁ እርሱ ይግዛኝ እገዛለሁ እንደ እግዚአብሔር መልካም አባት ወዴት አገኛለሁ አዝ:- እኔ የማመልከው ጌታዬ አባት ወንድም ጓደኛዬ የጸና ስሙ መሸሸግያዬ በፍቅሩ ተማርኬያለሁ ፍቅጄ አመልከዋለሁ ለዘላለም ለእርሱ እገዛለሁ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection