ለጻድቁ ክብር ክብር ይሁን የሚል ዝማሬ ከምድር ዳር ሲሰማ እኔም ድምፄን አብሬ አነሳለሁ ለእግዚአብሔር ክብር እዘምራለሁ ቅዱሳን መላዕክቱ ባንድነት ሌሊትና ቀንም ሚሰግዱለት የምድር ፍጥረታት ጉዑዛን ሁሉ ለቅዱሱ መንፈስ ይገዛሉ ደሙን አፍስሷልና እኔን ሊገዛ ለአዳኜ ኢየሱስ ምስጋናው ይብዛ (2x) ክብር ለእግዚአብሔር ክብር ለኢየሱስ ክብር ለመንፈስ ቅዱስ ሥሙ በዓለም ይንገስ (፲4x)