ጌታዬ አምላኬ ይዋሽ ዘንድ እንደሰው አይደለምና ላይችል ላይፈጽም ላይሞላ እንዲያው ቃል አይገባምና እርሱ ይሁን ያለው ይሆናል ቃሉ መች መሬት ጠብ ይላል የፍጥረት ሁሉ ገዢ ነው እንደወደደ ያደርጋል የጠራኝ ጌታዬ የታመነ ሁሉ እንደቃሉ የሆነ ምንተስኖት የማመልከዉ ለሀይሉ ወሰን የሌለዉ አዝ:- ጌታ እንደተናገረ እንዲሁ ስለሚፈጽመው ለነገ መጨነቄን ትቼ ዛሬ ምስጋናዬን እሰዋለሁ (2x) አብርሃምን ከዑር ሲያወጣው ወዶ ሲመርጠው ሲጠራው እንዲያው በከንቱ አይደለም ወደ ከነዓን የመራው በበረከቱ ባረከው በመታዘዙ አከበረው የተስፋ ቃሉን ፈጽሞ የትውልድ አባት አደረገው የጠራኝ ጌታዬ የታመነ ሁሉ እንደቃሉ የሆነ ምንተስኖት የማመልከዉ ለሀይሉ ወሰን የሌለዉ ሆ ሆ ሆ (8x) ምንተስኖት ምንተስኖት ምን አቅቶት ማን አግዶት እንደወደደ ያደርጋል ሰይጣንን ያንበረክካል (2x) አዝ:- ጌታ እንደተናገረ እንዲሁ ስለሚፈጽመው ለነገ መጨነቄን ትቼ ዛሬ ምስጋናዬን እሰዋለሁ (2x) አለቀ አበቃልኝ ብዬ መሰንቆዬንም ሰቅዬ ተቆርጧል ባልኩት ጉዳይ ከተፍ አለልኝ ጌታዬ ባህር ከፍሎ ስያሻግረኝ የረገጥኩትን ሲያወርሰኝ ስላየሁ ደግሞ ደጋግሞ በድል ተራራ ሲያቆመኝ ጌታ አሰራሩን አውርቼ ስለማልቸርስ አውርቼ ተመስገን ከማለት በቀር ሌላ ከቶ ምን ልናገር (2x)