አንዳንዴ ሳስታውስ የአለምን ኑሮዬን እንደተሰቃየሁ ሳላገኝ ጌታዬን ሰላም ስሻ ስከንፍ ስቀር በየቦታው ፈልጎ አዳነኝ የሰላሜ ጌታ አዝ:- እጄን ይዞ መራኝ ጌታዬ የዘላለም ባለውለታዬ አውጥቶኛል ከዓለም ገበያ በተራዬ ልበል ሃሌሉያ (2x) ሃ-ሌ-ሉ-ያ ሃ-ሌ-ሉ-ያ የጭንቀት ገደሌን ልወጣ ስቧትት ወጥቼ ወርጄ ተመልሼ ስወድቅ ልጁን ላከ ለኔ መጠለያ ሆነን ከረግረጉ ኃጢያት ባህር ወስጥ አወጣን አዝ:- እጄን ይዞ መራኝ ጌታዬ የዘላለም ባለውለታዬ አውጥቶኛል ከዓለም ገበያ በተራዬ ልበል ሃሌሉያ (2x) ሃ-ሌ-ሉ-ያ ሃ-ሌ-ሉ-ያ ስሙን ኢየሱስ አሉት አዳኝ ስለሆነ ከኃጢያት ልድኑበት እርሱ መረመረ እኔን አሰቃዩን እነርሱን ተዉአቸው ብሎ እነ ጴጥሮስን ከጉድ አወጣቸው አዝ:- እጄን ይዞ መራኝ ጌታዬ የዘላለም ባለውለታዬ አውጥቶኛል ከዓለም ገበያ በተራዬ ልበል ሃሌሉያ (2x) ሃ-ሌ-ሉ-ያ ሃ-ሌ-ሉ-ያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ በተራዬ ልበል ሃሌሉያ አውጥቶኛል ከዓለም ገበያ በተራዬ ልበል ሃሌሉያ