የጸና ግንብ ነው ያንተ ሥም ጌታዬ በመከራዬ ቀን ሆነኝ መጠጊያዬ ጻድቅ ሥምህን ጠርቶ ከጉዳት ያመልጣል ካስፈሪው ጨለማ ከጉድጓድ ይወጣል አዝ:- ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ መድኃኒቴ (2x) ሥምህ ከሥም ሁሉ በላይ ነው አምላኬ ፈጥነህ ትደርሳለህ ስጮህ ተንበርክኬ ከጨካኙ አውሬ ከሞት ኃይል ያድናል የሥምህ ጉልበቱ ጠላቴን ይጥላል አዝ:- ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ መድኃኒቴ (2x) ብዙዎች ተነሱ በኃይል የገነኑ ዝናቸው የናኘ ላፍታ ለሰሞኑ ዝንታለም አልቆዩም እንደጥላ አልፈዋል የኔ ጌታዬ ሥም ዛሬም ድንቅ ይሰራል አዝ:- ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ ወደ ኃይሉ ችሎት ገባሁ ያለከልካይ አጋፋሪ አልቆመ ዘበኛ ደጁ ላይ በጨነቀኝ ጊዜ በየትኛውም ቦታ ፊቱ አፈሳለሁ የእንባዬን ጠብታ የልቤን ብሶት ያያል ጩኸቴንም ያዳምጣል እንባዬን ያብስልኛል እንደንስር ያድሰኛል የጸና ግንብ ነው ያንተ ስም ጌታዬ በመከራዬ ቀን ሆነኝ መጠጊያዬ ጻድቅ ስምህን ጠርቶ ከጉዳት ያመልጣል ካስፈሪው ጨለማ ከጉድጓድ ይወጣል አዝ:- ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ መድኃኒቴ (2x) ሥምህን ሳነሳሳ ሰይጣን ይሸበራል ባንድ መንገድ መጥቶ በብዙ ይሸሻል በተኩላና በእባቡ ላይ እጫማለሁ አንበሳ ዘንዶውን እረጋግጣለሁ በጌታ እታመናለሁ ሥሙንም አውቀዋለሁ ስጠራው ይመልስልኛል ማዳኑንም ያሳየኛል ያከብረኛል (2x) መዝሙር ፩ (Mezmur 91) ዳዊት (ዳኒ) ወልዴ መዝሙር ፩ “በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉንም በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል እግዚአብሔርን አንተ መታመኝያዬ ነህ እለዋለሁ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው በእርሱ እታመናለሁ መዝሙር ፩ በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉንም በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል እግዚአብሔርን አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው በእርሱ እታመናለሁ (2x) አዝ:- ነፍሴን ከአዳኝ ወጥመድ ከአደገኛው መንገድ ከለሊቱ ግርማ ካስፈሪው ጨለማ በቀን ከሚበረው ከጠላት ፍላጻ በክንፎቹ ጋርዶ ሸሽጎኛልና በእርሱ እታመናለሁ ያስጥለኛል ስሙን አውቀዋለሁ ይጋርደኛል በመከራዬ ጊዜ ከእኔ ጋር ነው ታማኙን አምላኬን ላመስግነው ላመስግነው ላመስግነው እርሱ ታማኝ ነው (4x) አንዳንዴ እምነቴ ሲፈተንና ስታገል አቋራጭ መንገድ ስፈልግ ቶሎ ልገላገል ያን ጊዜ ይመጣና ቅዱስ ቃሉ ወደልቤ ፈጥኖ ይመልሰኛል ካልተቀደሰው ሃሳቤ አዝ:- ነፍሴን ከአዳኝ ወጥመድ ከአደገኛው መንገድ ከለሊቱ ግርማ ካስፈሪው ጨለማ በቀን ከሚበረው ከጠላት ፍላጻ በክንፎቹ ጋርዶ ሸሽጎኛልና በእርሱ እታመናለሁ ያስጥለኛል ስሙን አውቀዋለሁ ይጋርደኛል በመከራዬ ጊዜ ከእኔ ጋር ነው ታማኙን አምላኬን ላመስግነው (2x) ክብር (9x) ክብር ለርሱ ይሁን (3x) ክብር ለርሱ ይሁን (3x) ክብር ለርሱ ይሁን (3x) ክብር ለርሱ ይሁን (3x) ክብር ለንጉሡ (3x) ክብር ለንጉሡ (3x) ክብር ለርሱ ይሁን (3x) ክብር ለርሱ ይሁን (3x) ክብር ለንጉሡ (3x) ክብር ለንጉሡ (3x)