Song Lyrics

ይብዛልኝ መታዘዜ

Yibzalign Metazeze

Bereket Lemma
Yabokin Sishager
ግራና ቀኜን ላንተ ትጉ አድርገው ቀንሳለ ልሩጥህ መንግስትህን ላስፋው ደጆቼ ተከፍተው ብርሃኔም በርቶ የመንግስትህ ጉዳይ ያጥምደኝ በዝቶ ይብዛልኝ መታዘዜ ይብዛልኝ ላንተ መሮጤ ይብዛልኝ የመንግስትህ ጉዳይ ይክበደኝ ከሌላው በላይ ኢያኤል ያቺ ሴት ግራዋም ቀኙዎም ታዛዥ በድንኳን ከሚኖሩ ከሴቶች ይልቅ የተለየች ውሀ ለለመነ ወተት ሰጪ በከበረ ዳካ ሲሳራን የዘረረችው በእግሯ ስር አጋድማ ግራዋን ለካስማ ቀኝ እጇን ለመዶሻ በጥበብ የተሞላች ጠላትን የዘረረች የሆነች ታታሪ ለመንግስትህ ሰሪ የሆነች ሰራተኛ ለስራህ የማትተኛ ግራና ቀኜን ላንተ ታታሪ አድርገው ቀንሳለ ልሩጥህ መንግስትህን ላስፋው ደጆቼ ተከፍተው ብርሃኔም በርቶ የመንግስትህ ጉዳይ ያጥምደኝ በዝቶ ይብዛልኝ መታዘዜ ይብዛልኝ ላንተ መሮጤ ይብዛልኝ የመንግስትህ ጉዳይ ይክበደኝ ከሌላው በላይ በችግር በመከራ በፅናት ወንጌል ሰባኪ በድንጋይ ተወግሮ ማልዶ ለወንጌል ዘማች ግርፋት ደዌ ማያስቆመው በእፉኝት መነደፍ ዕለት ዕለት ሚያሳስበው የመንግስትህ መስፋት ሁልጊዜ ደስ የሚለው ታስሮ እንኳን የማይከፋው እንደ ጳውሎስ የጀገነ እስከ ሞት የቆረጠ የሆነ ሰራተኛ ለወንጌል የማይተኛ የሆነ ታታሪ ለመንግስትህ ሰሪ በዚች አጭር እድሜ መላኬን ዘንግቼ ለራሴ ጉዳይ እንዳይሆን ሩጫዬ ከእናቴ ማህፀን ጀምሮ ከለየኝ የኔ ብሎ እሮጣለሁኝ ከስጋ ከደም አልማከርም *2 ይብዛልኝ መታዘዜ ይብዛልኝ ላንተ መሮጤ ይብዛልኝ የመንግስትህ ጉዳይ ይክበደኝ ከሌላው በላይ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection