Song Lyrics

ትሁን ፈቃድህ

Tihun Fekadh

Bereket Lemma
Yabokin Sishager
አንተን አሳብቤ/አስታክኬ ለጥቅሜ የጸለይኩት ጸሎቴ ፊትህን ሳይሆን እጅህን እያየሁ የወሰድኩት መልሴ ህይወት ይሆናል ወይ ፊትህ ያልበራበት ምን ቢገኝ? ፀሎቴ ይገራ ልመናዬ ይመር መንፈስህ ያስተምረኝ አዝ ፡- ትሁን ፈቃድህ በኔ አይሁን እኔ ያልኩት ለኔ ስለ አባትነት ሳይሆን ስለ ክርክሬ ራርተህ ደጅህን ስለጠናሁኝ እዬዬ ማለቴን አይተህ ፀሎቴን እንዳትሰጠኝ ካልሆነ ያንተ ደስታ እንደ ቃየል ጠብቀኝ ብዬ ከፊትህ እንዳልወጣ አንተ የሌለህበትን ፊትህ ያልበራበትን አትስጣት ለነፍሴ ካንተ ሚለየኝን አንተ ሳትኖር በኔ ብትሰጠኝ ከነዓኔን በምን እለያለሁ ከሌላው ህዝብ እኔ ትሁን ፈቃድህ በኔ አይሁን እኔ ያልኩት ለኔ አትህድ ሰተኸኝ ከቤቴ ያዉልህ ብለህ ፀሎቴ አሳልፈህ ለኔ አትስጠኝ ደስ ያለህን ብቻ አድርግልኝ አትህድ ሰተኸኝ ከቤቴ ያዉልህ ብለህ ምኞቴ ለፈቃዴ እኔን አትስጠኝ ደስ ያለህን ብቻ አድርግልኝ ትሁን ፈቃድህ በኔ አይሁን እኔ ያልኩት ለኔ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection