ሆድ ሲብሰኝ ደግሞ ስትዘገይ የቀረህብኝ ሲመስለኝ ነብስ ስጋዬ ሲጨነቅ ለመቆም ስዝል ሲደክመኝ ብርታቴም ሲከዳኝ ስዳከም ጥያቄ ነብሴን ሲከባት መልስ እንኳን ባይኖረኝ ለነብሴ እንዳንተ ሚሆን ማን አላት የተማመንኩብህ አለ ያልኩህ ጌታ አንተን ተማምኜ የባሰ ቢመጣ ታምንሃለች ነፍሴ እርምጃ ቀርቶኝ ለሞት እጠብቅሃለሁ እስከመጨረሻ እስትንፍሴ ይስሀቅ ጠብቆህ የል በጌራራ ምንም በሌለበት ስፍራ ካንተ ጋር እሆናለሁ ስትለው አንተን አምኖ እንደዘራ መቼ ቀረ ታድያ በባዶ አንተን ጠብቆ ጠብቆ አጭዶ የለም ወይ መቶ እጥፍ ምድረበዳ ላይ ዘርቶ የተማመንኩብህ አለ ያልኩህ ጌታ አንተን ተማምኜ የባሰ ቢመጣ አምንሃለሁ ዛሬም እርምጃ ቀርቶኝ ለሞት እጠብቅሃለሁ እስከመጨረሻ እስትንፍሴ አብርሀምም ወጣ ከካራን የተገለጠለትን አምኖ ድንኳኑን ተከለ ምድረበዳ እንደመፃተኛ ሆኖ ሙት እንኳን ከሆነው ከስጋው ከ ደከመ ጉልበቱ አምኖህ የለም ወይ ያለምክኒያት የሚያስክድ ሰበቡን ትቶ የኔና ያንተ መዋደድ የኔና ያንተ ቁርኝት ከምክኒያት ከሰበብ አልፎ ሆኖ የል ያለ ልክ ያለ ምስክር ማስረጃ እንዳመነህ እንደ አብርሐም የኔም ልብ በአንተ ላይ እንደዛው ፀንቶአል አመንኩህ ከኔ ጥያቄ አመንኩህ በጎደለኝ አመንኩህ ቀረኝ ከምለው አመንኩህ በቃ ወደድኩህ