ሳይቆረቁረኝ ትከሻው ሳይታክት እጄን ሲይዘኝ ብዙም አልታዘዝኩም ከአመታት አመት ሳልሰማው ኖርኩኝ ልቤማ ጠጣር ነው ለመርታት እንጂ መሸነፍ መች አውቆ ከያቦቅ ማዶ ብቻዬን አስቀረኝ ሊያሸንፈኝ ወዶ ብዙ ባክኛለሁ እርካታን ፍለጋ ደሞዜን ቀይረው ሲያስከፍሉኝ ዋጋ ብቻዬን ስሞግት ሊነጋ ሲያቅላላ አንዴ ንካኝና ጎዶሎዬን ሙላ ላንተ ተሸንፌ ሌላውን አሸንፌ በድሌ መዝገብ ላይ ልፃፍህ አድምቄ አንዴ ነክተኸኝ ስሜን ከለወጥከው እያነከስኩም ቢሆን ሁሉንም ቀድማለሁ ቀድሜ ደርሳለሁ ያቦቅን ስሻገር ተሸንፌ ነው አንተ ግን ያልከኝ አሸንፈህ ነው አርፍጄ ስሻገር ተሸንፌ ነው አንተ ግን ያልከኝ አንተ ቀድመህ ነው *2 አሁን አልዋሽህም ስሜን ነግርሃለው ሰብስቤ ሲበተን ስባክን ኖረያለሁ ይሻግር ደሞዜም የልፋቴም ዋጋ ብቻዬን ቀርቼ ልሞግት ካንተ ጋር ንካው ሹላዳዬን ቀደም ቀደም አልበል አንተን አስቀድሜ ከኋላ ልሻገር እያነከስኩ ብመጣም ፈጥኜ ባልኸድም ካንተ ጋር ዘግይቶ ያረፈደ የለም የከሰረ የለም ያቦቅን ስሻገር ተሸንፌ ነው አንተ ግን ያልከኝ አሸንፈህ ነው አርፍጄ ስሻገር ተሸንፌ ነው አንተ ግን ያልከኝ አንተ ቀድመህ ነው *2 ያልቀደመኝ የለም ያላለፈኝ እኔን በምህረት ደጅ ስጠብቅ ዘመዴን መቀደም ተምሬ መረታት ሰው ከሌለህ መጠበቂያው ስፍራው ሆኖኝ መኖርያዬ እድሜዬን ከስሬ ለማላተርፍበት ከሰው ተገልዬ ተገናኘን ድንገት ልሸከም ችላለሁ የተሸከመኝን አንዴ ንካኝና ስሜን ለውጥልኝ ስፍራ ለውጥልኝ ሰው የለኝም ስልህ ተቀድሜ ነው አንተ ግን ምትለኝ እኔ እስክመጣ ነው ምሬቴን ስነግርህ ተሸንፌ ነው አባ ግን ምትለኝ እኔ እስክመጣ ነው