Song Lyrics

አመልክሃለሁ

ሞልቶ ለማይሞላ ለዚህ ዓለም ጉዳይ (2x) ጊዜ አላጠፋም ጐዶሎዬን ሳይ (2x) የበረከት ምንጩ መንገዱ ገብቶኛል (2x) ሁኔታው እያለ አምልከኝ ብሎኛል (2x) ልቤም እንዲህ ይለኛል ኧረ ተነስ ይለኛል አምልክ አምልክ ይለኛል አመልክሃለሁ ጌታዬ አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ ኢየሱስ አመልክሃለሁ (2x) ተይ አልኳት ነፍሴን ተይ እንጂ (2x) ኢየሱስ ቆሞ ከደጅ መዘመር ማምለክ ነው እንጂ (2x) አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ዛሬም መጣሁ ወደ ደጅህ ምህረትህ በዝቶልኝ በሕይወቴ ያቆመኝ ፀጋህ ነው መድኃኒቴ አሁን አሁንማ እየዋለ ሲያድር (2x) ይገርመኝ ጀመረ የመስቀሉ ፍቅር (2x) ልቤን ያደረገው የዝማሬ ጓዳ (2x) ለካስ ተምሬ ነው የለብኝም ዕዳ (2x) ልቤም እንዲህ ይለኛል ኧረ ተነስ ይለኛል አምልክ አምልክ ይለኛል አመልክሃለሁ ጌታዬ አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ ኢየሱስ አመልክሃለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection