Song Lyrics

የእኔማ

የእኔማ የእኔማ ሰላም የእኔማ የእኔማ የእኔማ ደስታ የእኔማ ( 2x) ከዚህ ዓለም አይደለም በመንፈሱ ነው በብርም በወርቅም የማይገዛው በወንጌል ሞኝነት በአመንኩት ቃል ሰላሙ ከሆዴ ይፍለቀለቃል አገዘኝ አገዘኝ (፰x) ጠላቴ ዓይኑ እያየ በመንፈሱ ነካኝ አትረፈረፈኝ አገር ምድሩ እያየ በቅባቱ ነካኝ አትረፈረፈኝ አገዘኝ አገዘኝ (፰x) ላምልክህ ደግሜ እስኪ ደግሜ ደጋግሜ (አሄ) ላምልክህ ደግሜ እስኪ ደግሜ ደጋግሜ ( 2x) ይውጣ ወደላይ ከድንኳኔ የአምልኮ የዝማሬው ቅኔ የሆንክልኝን ሳስበው ከዚህ በላይ ምን አለ ምሆነው ከፍ በልልኝ (፬x) ደምቀህ ታይልኝ (፬x) ና ሲለኝ ቃሉን ተማምኖ በውኃው ላይ ና ሲለኝ እጁእንደማይጥል አታዩም ወይ ና ሲለኝ ከሁኔታ ጋር እርሱ አይለካ ና ሲለኝ መንገድ ይሆናል ውኃውም ለካ ጠላቴ ዓይኑ እያየ በመንፈሱ ነካኝ አትረፈረፈኝ አገር ምድሩ እያየ በእሳቱ ነካኝ አትረፈረፈኝ አገዘኝ አገዘኝ (፰x) የእኔማ የእኔማ ሰላም የእኔማ የእኔማ የእኔማ ደስታ የእኔማ ( 2x) ከዚህ ዓለም አይደለም በመንፈሱ ነው በብርም በወርቅም የማይገዛው በወንጌል ሞኝነት በአመንኩት ቃል ሰላሙ ከሆዴ ይፍለቀለቃል አገዘኝ አገዘኝ (፰x) ላምልክህ ደግሜ እስኪ ደግሜ ደጋግሜ (አሄ) ላምልክህ ደግሜ እስኪ ደግሜ ደጋግሜ ( 2x) ይውጣ ወደላይ ከድንኳኔ የአምልኮ የዝማሬው ቅኔ የሆንክልኝን ሳስበው ከዚህ በላይ ምን አለ ምሆነው ከፍ በልልኝ (፬x) ደምቀህ ታይልኝ (፬x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection