Song Lyrics

ፅላት

ከእስትንፋሴ ይልቅ ኦሆ የምትቀርበኝ እንደ ዓይንህ ብሌን ኦሆ የምጠብቀኝ ብቻዬን ነኝ ብዬ ኦሆ የቆዘምኩ ለታ ፍቅርህ ይሰማኛል ኦሆ አልፏ የእኔን ሁኔታ በልቤ ፅላት ላይ ያረፈው ፍቅርህ ይቀሰቅሰኛል ሀሌሉያ ሁሌ እንዳመልክህ በልቤ ፅላት ላይ ያረፈው ፍቅርህ ይቀሰቅሰኛል ሁሌ እንዳመልክህ ኦሆሆሆሆሆ ላምልክ (፰x) አይደክመኝም በቃ አምልኬ አምልኬ ልብህ እስኪረካ የኔንም መስዋእት የፃፍኩትን መዝሙር ወደኀዋል ለካ የቀረው ዘመኔ ይለቅ በፊትህ አንተን እያመለኩኝ እያከበርኩህ እንዴት ብዬ ላምልክ ( 2x) ኧረ እንዴት ብዬ ላምልክህ ውለታህን ሳስበው መግለጫ ቃላት አጣሁ አዎ ያንትን ፍቅር ሳስብ መግለጫ ቃላት አጣሁ አዎ በጨለማው ሀገር ኦሆ ሀጥያት ክብዶብኝ ማነው ከዚህ ስቃይ ኦሆ የሚያሳርፈኝ በሞት ተከብቤ ኦሆ ግራ ገብቶኝ ሳለ በፍቅርህ አድነህ ኦሆ ታሪኬን ለወጥከው በልቤ ፅላት ላይ ያረፈው ፍቅርህ ይቀሰቅሰኛል ሀሌሉያ ሁሌ እንዳመልክህ በልቤ ፅላት ላይ ያረፈው ፍቅርህ ይቀሰቅሰኛል ሁሌ እንዳመልክህ ኦሆሆሆሆሆ ላምልክ (፰x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection