አንዳንዴማ ሆዴን ባር ባር ሲለው ብቸኝነት ይዞኝ አንዳንዴማ የልብ ወዳጅ ያልኩት ከጐኔ ሲርቀኝ (2x) አዝናለሁ ሰው ነኝና (2x) የቀረው ግን ይቅርብኝ አስቤ ልበል ቀና (2x) በዚህ ዓለም ስኖር ከአንተ ጋር አንዴ ይሞላል ይጐላል አንተ ከጐኔ ስላለህ ምን ያሰጋኛል (2x) አሃ አንዴ ይሞላል አንዴ ይጐላል አሃሃ አንተ ስላለህ ምን ያሰጋኛል አሃ ቀኑ ይመሻል ቀኑ ይነጋል አሃሃ አንተ ስላለህ ምን ያሰጋኛል ጐዳናው ብዙ ነው በሰው በሰው ልብ ውስጥ ያለው ትላንትናን ኖሮ ዛሬ ምኞት አለው (2x) ደግሞ ይናፍቀኛል ፊትህ ይናፍቀኛል (4x) አንዳንዴማ ሆዴን ባር ባር ሲለው ብቸኝነት ይዞኝ አንዳንዴማ የልብ ወዳጅ ያልኩት ከጐኔ ሲርቀኝ (2x) አዝናለሁ ሰው ነኝና (2x) የቀረው ግን ይቅርብኝ አስቤ ልበል ቀና (2x)