አገኘሁ መላ ያለበት ቤት አገኘሁ ፍርድ የሚሰጥበት ለዚህ ነው የተረጋጋሁት (2x) ልዑል ነው ልዑል ነው አባቴ (2x) ዝማሬው ይፈልቃል ከቤቴ እንዴት ይመኛል ልቤማ ሌላ ተስተናግጄ ከንጉሥ ጋራ ተቆረሰና የሰላም ማዕድ ቤቱ ይሞቃል አያስገባም ብርድ አሃ አሃ ለተጨነቀማ ግራ ለገባዉ ትክክለኛው መልስ በእጁ ነው ያለው (2x) ተራራው ተጋርዶ ፊት ለፊት ሳየው ጌታ እንዳስለመደኝ እጄን አነሳሁ በመንፈስ የሆንን አምልኮን ስሰዋ የት እንደ ሄደ አላውቅም ወዴት እንደገባ የእኔ ጌታ የእኔ እረኛ ለዚህ እኮ ነው የጠራኛ/የቀባኛ (2x) ሊነካኝ አይችልም ጠላቴ (2x) እሳቱ ከቦኛል የአባቴ አትንኩት አትንኩት ይላሉ (2x) ይታያል ደሙ በጉበኑ አትንኳት አትንኳት ይላሉ አትንኩት አትንኩት ይላሉ ይታያል ደሙ በጉበኑ ጳውሎስና ሲላስ ቢታሰር እጃቸው አምልኮ አላቆሙም ተፈቷል ውስጣቸው ሊጠፋ አይችልም ውስጥ ያለው እሳት እንደውም ይብሳል ሲቆሰቁስት የእኔ ጌታ የእኔ እረኛ ለዚህ እኮ ነው የቀባኛ/የጠራኛ (2x) ወዴት ወዴት ወዴት (2x) እንዴት እንዴት ይመኛል እንዴት እንዴት እንዴት የንጉሥ ቤተሰብ አይመኝም ሌላ አምሮበት ይኖራል ከእጁ እየበላ የንጉሥ ቤተሰብ አይመኝም ውጪ ያበድራል እንጂ አይደለም ተረጂ የእኔ ጌታ የእኔ እረኛ ለዚህ እኮ ነው የጠራኛ/የቀባኛ (2x)