የሕይወቴን ጅማሬ የሕይወቴን ፍጻሜ ባረከልኝና የትላንቱ ኑሮዬን የትላንቱ ኃጢአቴን ይቅር አለኝና ኑር አለኝ (3x) ጌታ ኑር አለኝ ኑር አለኝ (3x) ጌታ ኑር አለኝ ልዑል ዓላማ አለው በእኔ ላይ (2x) በእኔ ላይ (4x) ልዑል ዓላማ አለው በእኔ ላይ (2x) በእኔ ላይ (4x) በጉዞዬ ግራ እንዳይገባኝ በሌሊትም በቀን ስትመራኝ በደመናው በእሳትህ አምደህ ተከተልከኝ ልቤ . (1) . ኢየሱስ ስልህ ውድዬ ስልህ አግዘኝ ስልህ ና እርዳኝ ስልህ ማዕበሉን ረግጠህ ትመጣልኛለህ ወጀቡን ረግጠህ ትደርስልኛለህ ማዕበሉን ረግጠህ ትመጣልኛለህ ወጀቡን ረግጠህ ትደርስልኛለህ (2x) በገና አንስቼ የትንቢት ዜማ ስደረድር ማምለኬን አውቆ ውኃ ፈለቀ ደረቅ ምድር ዓይኔን ሲከፍተው ልቤን ሲከፍተው ዙሪያዬን ሳይ ኢየሱስ ቆሟል ጠላቴ ደፍሮ እንዳይነካኝ ልዑል ዓላማ አለው በእኔ ላይ (2x) በእኔ ላይ (4x) ልዑል ዓላማ አለው በእኔ ላይ (2x) በእኔ ላይ (4x) ምዕራፌ እንዳይዘጋ የጨለመው ቶሎ እንዲነጋ በበረሃው ጥላ የሆንከኝ አንተ እኮ ነህ ከሞት ያዳንከኝ ኢየሱስ ስልህ ውድዬ ስልህ አግዘኝ ስልህ ና እርዳኝ ስልህ ማዕበሉን ረግጠህ ትመጣልኛለህ ወጀቡን ረግጠህ ትደርስልኛለህ ማዕበሉን ረግጠህ ትመጣልኛለህ ወጀቡን ረግጠህ ትደርስልኛለህ (2x)