Song Lyrics

ይደክመኛል መኖር

የሕይወቴ እረኛ ጌታ አለልኝ የማይተኛ (2x) የሕይወቴ ጠበቃ ጌታ እኮ ነው እንዳልሰጋ (2x) እኔማ ዕድለኛ ነኝ አልፈራም ጌታ ስላለኝ ዓለቱ ነው መሠረቴ አይወድቅም በንፋስ ቤቴ ከኢየሱስ ጋር ተዋድጄ ይፈልቃል ሰላም ከደጄ ለካ ለካ ጌታ እኮ ነው (2x) የትላንቱን ያንን ወጀብ ፀጥ ያረገው (2x) ኧረ እኔ አመል ሆኖብኛል አመል (2x) ስነሳ ስቀመጥ ለክብርህ መዘመር እንደዚህ ካልሆነ ይደክመኛል መኖር የእኔ ነህ (2x) የእኔ ነህ ብልህ ከመሞት/ከጭንቀት ያዳንከኝ ጌታዬ እኮ ነህ (2x) ከእንግዲህማ ወዳጅ አግኝቻለሁ ከእንግዲህማ አብሮ የሚዘልቅ ከእንግዲህማ እንዲህ ከወደደ ከእንግዲህማ ጥሎ የማይሄድ (2x) የሕይወቴ እረኛ ጌታ አለልኝ የማይተኛ (2x) የሕይወቴ ጠበቃ ጌታ እኮ ነው እንዳልሰጋ (2x) እኔማ ዕድለኛ ነኝ አልፈራም ጌታ ስላለኝ ዓለቱ ነው መሠረቴ አይወድቅም በንፋስ ቤቴ ከኢየሱስ ጋር ተዋድጄ ይፈልቃል ሰላም ከደጄ ለካ ለካ ጌታ እኮ ነው (2x) የትላንቱን ያንን ወጀብ ፀጥ ያረገው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection