Song Lyrics

እውነተኛ ወዳጅ

ከመፈጠሬ ከመታሰቤ ጀምሮ የማትለወጥ የማትቀየር ወረት የሌለበት አንተን ነው ያየሁት (2x) አዝ፦ እውነተኛ ወዳጅ ነህ እውነተኛ አፍቃሪ (2x) የእኔስ ወዳጅ አንተ ነህ ጊዜ/ዘመን የማይለውጥህ (2x) ለካስ ሁሉም ነገር ያልፋል ለካስ አለው መጨረሻ ለካስ እኔስ ወዳጅ አለኝ በቃ ክፉ ቀን ማሸሻ የሰው ልጅ ሆኖ የሰው እየተባለ ማነው ከሰማይ መጣ ከላይ አላስችል ብሎት ሲያይ ከሞት አወጣኝ ከሞት ደርሶልኝ ካለሁበት ተናገር ምንድን ነው ሲሉኝ ለዚህ ነው ቃላት ያጠረኝ ሰማይ ይናገር ምድርም ስላንተ ላውራ ዘለዓለም (2x) አዝ፦ እውነተኛ ወዳጅ ነህ እውነተኛ አፍቃሪ (2x) የእኔስ ወዳጅ አንተ ነህ ጊዜ/ዘመን የማይለውጥህ (2x) ለካስ ሁሉም ነገር ያልፋል ለካስ አለው መጨረሻ ለካስ እኔስ ወዳጅ አለኝ በቃ ክፉ ቀን ማሸሻ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection