Song Lyrics

ጌታ አለኝ

አምላኬ ነው የደገፈኝ እንዳልወድቅ በድካሜ በሃሩሩ ጥላ ሆኖ ሳይለየኝ ከአጠገቤ ከኋላዬ ሲከተለኝ እንቅፋቱ እንዳይጐዳኝ የጠላዬን ወጥመድ ሰብሮ መኖሪያዬ ሆነልኝ አሃ ሲከተለኝ አሃ ከኋላዬ አሃ ሆኖልኝ ነው አሃ ከለላዬ አሃ ቀኑ ሲከፋ አሃ ሲጨልም አሃ ወንድም አለኝ አሃ አይዞህ የሚል ጌታ አለኝ (፲2x) ቅጥር ሆኖልኝ ነው እኔስ ያለፍኩት አላልፈው ነበር ባይኖረኝ አባት የትላንቱ ያን ጨለማ ይገርመኛል ኧረ እንዴት (2x) እንዴት ጠፋ ሰባት እጥፍ የነደደው እሳት ጠፍቷል ጌታዬን (2x) ላመስግነው ዋስትናዬ ሆኗል ለእኔ ጌታ (4x) ከለላዬ ሆኗል ለእኔ ጌታ (4x) የትላንቱን ያንን ወጀብ ቆም ብዬ ሳስበው የዛሬን ቀን ስላየልኝ ፀጥ ያረገው ጌታ ነው ለነገማ ዋስትና አለኝ ንፋስ ቢነፍስብኝ እላዬ ከእንግዲህማ ልቤ አይፈራም ጌታ እኮ በታንኳዬ አሃ ሲከተለኝ አሃ ከኋላዬ አሃ ሆኖልኝ ነው አሃ ከለላዬ አሃ ቀኑ ሲከፋ አሃ ሲጨልም አሃ ወንድም አለኝ አሃ አይዞህ የሚል ጌታ አለኝ (፲2x) ቅጥር ሆኖልኝ ነው እኔስ ያለፍኩት አላልፈው ነበር ባይኖረኝ አባት የትላንቱ ያን ጨለማ ይገርመኛል ኧረ እንዴት (2x) እንዴት ጠፋ ሰባት እጥፍ የነደደው እሳት ጠፍቷል ጌታዬን (2x) ላመስግነው ዋስትናዬ ሆኗል ለእኔ ጌታ (4x) ቤተኛዬ ሆኗል የእኔ ጌታ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection