አትተወኝ እባክህ አትራቀኝ መንፈስህን ከውስጤ አትውሰደው (2x) ደግሞ እንደሚያውቅ እንደሚያውቅ ልብ እንዳለው ብዙ ደከምኩኝ እራሴን ታዝቤያለሁ (2x) አዝ፦ ይቅርታ ይቅርታ የእኔ አባት ይቅርታ ይቅር በለኝና አስገባኝ ዳግም ወደ ጉያህ (2x) ያኔ ያኔ አንተን ያወኩበት የልጅነት ኩራት አይደክመኝም ፊትህን ስፈልግ ጠዋት ሆነ ማታ ምነው አሁን ልቤን ምን አገኘው ምን ገባብኝ ቆም ብዬ ራሴን ልጠይቀው ምህረት አርግልኝ ወደ አይምሮዬ ልመለስና ማረኝ ልበለው በርከክ ልበልና (2x) አዝ፦ ይቅርታ ይቅርታ የእኔ አባት ይቅርታ ይቅር በለኝና አስገባኝ ዳግም ወደ ጉያህ (2x)