Song Lyrics

አየሁት

አየሁት አየሁት ያየኝን ጌታ አየሁት አየሁት እጄን ይዞኝ አየሁት አየሁት በምድረ በዳ አየሁት አየሁት እየመራኝ እየመራኝ /4 በዛ በለሊት ያሳኝ ህልም ተፍጽሟል እኮ ቅዠት አይደለም በዛ በለሊት የሰጠኝ ቃል ተጽሟል እኮ አንድም: ሳይጎል አለልኝ አለልኝ /4 ከአንተ ጋር ስኖር ከጥላህ ሥር ኃይሌ ታደሰ እንደ ንስር ልቤን ጠበከው ቅጥር ሆነኸኝ አቤት ይገርማል ስንቱን አለፍኩኝ አዎ ጥዋት ስነሳ ፊትህ ቀርቤ እቀበልና ፀጋ ደርቤ ቀኑን በሙሉ የዝማሬ ቃል አዳዲስ ቅኔ ከአፌ ይፈልቃል በቃ በቃ ክረምቱ አለፈ በቃ በቃ የዝማሬው ቃና ሸተተኝ በቃልኝ ክረምቱ አለፈ በቃልኝ አለፈልኝ /3 ደረሰልኝ ደረሰልኝና /2 ተለወጠ ታሪኬ እንደገና የአመንኩት ጌታ እይጥልም ብዬ ለቅሶየን ተካው በአዲስ ዝማሬ/ 2 አይጥም አይጥልም አይጥልም :'አሀሀ ሰው ያደርጋል እንጂ አይጥልም ቃሉ ጠበቀኝ እንዳልዋጥ በውሃ ሳልፍ በሳቱ ውስጥ አላቃጠልኝ አልሰጠምኩኝ እጆቼን ይዞ ስላገዘኝ የተናገረኝ የትንቢቱ ቃል ያንን ክፉ ቀን አሳልፎኛል ከዓለቱ ውስጥ: ከዚያ ጨለማ ወጥቼ ዛሬ ድምጼን ላሰማ በቃ በቃ ክረምቱ አለፈ በቃ በቃ የዝማሬው ቃና ሸተተኝ በቃልኝ ክረምቱ አለፈ በቃልኝ አለፈልኝ /3
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection