Song Lyrics

የተስፋ ቃል

የተስፋ ቃል ሰጠኝ ገና በልጅነት እኔ አለሁ አለኝ ሃሩሩ እንዳይጐዳኝ እባቡ እንዳይነድፈኝ እንዳይጠጋኝ አቤት የተነሳው የጠላት ዘመቻ ገፍቶ ሊጥለኝ የእርሱ ቤት ደካማ የእኔ ግን በጌታ ሄደ እየበረታ የእኔ ዳኛ ከጐኔ ነበር ( 2x) ከጐኔ (ከጐኔ ከጐኔ) የእኔ ዳኛ ከጐኔ ነበር ( 2x) ከጐኔ (ከጐኔ ከጐኔ) የእኔ ዳኛ ከጐኔ ነበር ( 2x) ከጐኔ (ከጐኔ ከጐኔ) ገና (፫x) ገና ነው ገና (፫x) ነው ገና ነው የአባቴ ስራ ገና ነው በእኔ የጀመረው ገና ነው መቼ ተፈጸመ ገና ነው ማነው ቆሟል ያለ ( 2x) በእጄ ላይ ያለው በትር ከሆነማ ባሕሩን ምታው ለአንተ መንገድ አለ ከሁኔታ በላይ አብ ያዘጋጀው ዛሬ የከበደህ ያስደነገጠኽን የግብጹን ጦረኛ በመዝሙር ልጣለው ጆሮዎችህን ስጠኝ ና ተባበረኛ (አሃሃሃሃሃ) መንፈሱ በላዬ አሁን መጣብኝ (አሃሃሃሃሃ) ያለህበት ችግር ግልጽ ሆኖ ታየኝ (አሃሃሃሃሃ) ለዚህማ አምልኮ ምሥጋና ነው መልሱ (አሃሃሃሃሃ) አሁን ተነሳልህ ኢየሱስ ንጉሡ ወደቀልህ ሰንሰለቱ በኢየሱስ በክንደ ብርቱ ወደቀልህ በሽታው ለዘላለም እንዳታየዉ መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይለኛል እንዲህ ይለኛል እንዲህ ይለኛል ( 2x) ገና (፫x) ገና ነው ገና (፫x) ነው ገና ነው የአባቴ ስራ ገና ነው በእኔ የጀመረው ገና ነው መቼ ተፈጸመ ገና ነው ማነው ቆሟል ያለ ( 2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection