Song Lyrics

የሕይወቴ እረኛ

Awtaru Kebede
Tenestoal
እኮ አንተ የሕይወቴ መሪ ነህ አንተ የሕይወቴ እረኛ ነህ ልቤን ለአንተ ትቼዋለሁ ዘለዓለም አምልክሃለሁ (3x) እውነትን ልናገር አይዋሽ አንደበቴ ውስጤን ያሳረፈው ኢየሱስ ነው አባቴ ሁሉንም አስናቀኝ እኔም ሁሉን ተውኩት ጌታዬ እንደሚሻል ውስጤን አሳመንኩት አዝ፦ አለኝ ልበል እኔ አለኝ ልበል አለኝ ልበል አባት ውስጤ ያረፈበት/የኮራበት (2x) ከሲና መጣ የእግዚአብሔር ክብር ሕግን ሊያወጣ ለዚች ለምድር በእራሱ ፈቃድ የሚጓዘውን ሕዝብ በእግዚአብሔር ፀጋ እንዲተዳደር ካለፈው ኪዳን የሚሻል ኪዳን የእግዚአብሔር ክብር ኢየሱስ መጣ በሰው ጫንቃ ላይ የተቀመጠው ቀንበር ተፈታ አዝ፦ አለኝ ልበል እኮ አለኝ ልበል አለኝ ልበል አባት ውስጤ ያረፈበት (2x) እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝም የለም ። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል በእረፍቱ ውኃ ዘንድ ይመራኛል ። ነፍሴን መለሳት ስለ ሥሙም በፀድቅ መንገድ መራኝ ። [1]
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection