Song Lyrics

የግሌ ነህ

Awtaru Kebede
Tenestoal
አዝ፦ የግሌ ነህ ለእኔ ሙኩሪያ መመኪያዬ አይቆረቁረኝም ትከሻህ ጌታዬ አሃሃ ትከሻህ ጌታዬ የፀሐዩን ብርታት በጥላህ ከልክለህ ኑሮን እኖራለሁ ሳልሳቀቅብህ አሃሃ ሳልሳቀቅብህ ለታላቅነትህ ሲወራ ሲተረክ ቃላቶች አቅም አጠራቸው ለመግለጽ ከሰማያት በላይ በላይ አንተ ታላቅ ነህ ከምድርም በታች በታች አንተ ታላቅ ነህ እንደ ገለፅክልን ሥምህን ልባርክህ (2x) አዝ፦ የግሌ ነህ ለእኔ ሙኩሪያ መመኪያዬ አይቆረቁረኝም ትከሻህ ጌታዬ አሃሃ ትከሻህ ጌታዬ የፀሐዩን ብርታት በጥላህ ከልክለህ ኑሮን እኖራለሁ ሳልሳቀቅብህ አሃሃ ሳልሳቀቅብህ አትታማም ክፉ አድርገሃል ተብለህ ለልጆችህ ሁሌ መልካም ነህ ከማደሪያህ ቃል ትልካለህ የዛለን ልብ ታሳርፋለህ አምላክ ነህ ጌታዬ (2x) ንጉሥ ነህ ጌታዬ (2x) ኃያል ነህ ጌታዬ (3x) አዝ፦ የግሌ ነህ ለእኔ ሙኩሪያ መመኪያዬ አይቆረቁረኝም ትከሻህ ጌታዬ አሃሃ ትከሻህ ጌታዬ የፀሐዩን ብርታት በጥላህ ከልክለህ ኑሮን እኖራለሁ ሳልሳቀቅብህ አሃሃ ሳልሳቀቅብህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection