ይህንን ጌታ ነው ጌታዬ ነህ ያልኩት ጨለማውን አይቶ ልቡ የማይደነግጥ (2x) የችሎቱ ብዛት እጅግ ይገርመኛል ውኃውን እረግጠህ ና እንጂ ና ልጄ አትፍራ ይለኛል (2x) አትፍራ ይለኛል አዝ፦ እስከሚሆን ድረስ ብቻ አላምንህም እስከመጨረሻው አትችልም አልልም ውኃውን እረግጠህ ማን ጀግና ና ይላል ከብዙ አማልክት የእኔ ጌታ ለየት እኮ ይላል ለየት እኮ ይላል ለየት ለየት እኮ ይላል (2x) አልመዝንህም ስለሆነና ስላልሆነ እምነቴ ዛሬም ትኩስ ነው መች ቀዘቀዘ አያሳልፍም እኔስ አልልም ውኃውን አይቼ ቀጥ ያለ መንገድ ይሆናል ስላለ ጐኔ አዝ፦ እስከሚሆን ድረስ ብቻ አላምንህም እስከመጨረሻው አትችልም አልልም ውኃውን እረግጠህ ማን ጀግና ና ይላል ከብዙ አማልክት የእኔ ጌታ ለየት እኮ ይላል ለየት እኮ ይላል ለየት ለየት እኮ ይላል (2x) በእኔ ውስጥ ያለው ይሄ ኢየሱስ መቼ ደክሞ ያውቃል ግራ አይገባው እንደ ሰው የት ይሸበራል ብቻ ከፊቴ ችግር ሲጋረጥ እንዲህ ይለኛል መፍትሄ የአንተ ነው ተሻገር እንጂ እረፍ ይለኛል አዝ፦ እስከሚሆን ድረስ ብቻ አላምንህም እስከመጨረሻው አትችልም አልልም ውኃውን እረግጠህ ማን ጀግና ና ይላል ከብዙ አማልክት የእኔ ጌታ ለየት እኮ ይላል ለየት እኮ ይላል ለየት ለየት እኮ ይላል (2x) ደመናን አይቶ ትንቢት መናገር ሁሉም ይችላል ንፋሱ ሲነፍስ ሰው ሁሉ ይዘንባል ይላል የእኛ ጌታ ግን ለየት ያለው ነው ትንቢት ሲናገር ውኃን ያመጣል እንዲሁ ደመና ሳይኖር አዝ፦ እስከሚሆን ድረስ ብቻ አላምንህም እስከመጨረሻው አትችልም አልልም ውኃውን እረግጠህ ማን ጀግና ና ይላል ከብዙ አማልክት የእኔ ጌታ ለየት እኮ ይላል ለየት እኮ ይላል ለየት ለየት እኮ ይላል (2x)