አዝ፦ አልገፋ ያልውን ቀን ክንድህ ገፍቶት አሻገርከኝ ሁሉን ችዬ በአንተ አለፍኩ መቸገሬን አስረሳኸኝ ማን ልበልህ ምን ልበልህ ምላሽ አጣሁ ጌትዬ የምከፍልህ አዎ ዝቅ ብዬ ክብሬን ጥዬ ልስገድልህ ጌታዬ ተዋርጄ (2x) ከኋላዬ ርቆ እንደ ህልም አለፈ እንደ ፈሳሽ ውኃ መጨነቄ ሄደ (2x) ምሥጋናዬ አርጐ መቅደስህን ይሙላው ለውለታህ ምላሽ ይሄም ሲያንስብህ ነው (2x) አዝ፦ አልገፋ ያልውን ቀን ክንድህ ገፍቶት አሻገርከኝ ሁሉን ችዬ በአንተ አለፍኩ መቸገሬን አስረሳኸኝ ማን ልበልህ ምን ልበልህ ምላሽ አጣሁ ጌትዬ የምከፍልህ አዎ ዝቅ ብዬ ክብሬን ጥዬ ልስገድልህ ጌታዬ ተዋርጄ (2x) እጅህ እየረዳኝ ሁሉን ተሻገርኩ አልገፋ ያለውን ቀኖቼን አለፍኩ (2x) ለአደረከው ሥራ ምሥጋና ይገባሃል ነፍስ ያለው ግዑዙ ወድቆ ይሰግድልሃል (2x) አዝ፦ አልገፋ ያልውን ቀን ክንድህ ገፍቶት አሻገርከኝ ሁሉን ችዬ በአንተ አለፍኩ መቸገሬን አስረሳኸኝ ማን ልበልህ ምን ልበልህ ምላሽ አጣሁ ጌትዬ የምከፍልህ አዎ ዝቅ ብዬ ክብሬን ጥዬ ልስገድልህ ጌታዬ ተዋርጄ (2x) ምን ቢሰጥህ ምላሽ የአንተን ሥራ ይተካል እንዲያው ዝቅ ብሎ ማመስገን ይሻላል (2x) እስከ ምድር ዳርቻ የሚመስልህ ታጥቷል ትልቁ እግዚአብሔር ክብር ይገባሃል (2x) የእኔ ኢየሱስ የእኔ አባት የእኔ ጌታ አንተ ነህ የእኔ ባለ ውለታ (2x) ላብዛልህ አምልኮ ላብዛልህ ላብዛልህ ስግደትም ላብዛልህ (2x) የእኔ ኢየሱስ የእኔ አባት የእኔ ጌታ አንተ ነህ የእኔ ባለ ውለታ (2x) ላብዛልህ አምልኮ ላብዛልህ ላብዛልህ ስግደትም ላብዛልህ (2x)