በምድረ በዳ ላይ ማኖር ልማዱ ነው (2x) እስቲ ልፎካከር በሰሜን በደቡብ በምስራቅ በምዕራብ እርሱ ነው እግዚአብሔር (2x) ትልቅ ነው ብዬ መታሁት እንጂ መቼ ፈራሁት በበረሃ ውስጥ አስተምሮኛል ኑሮ የእኔ አባት (2x) የተደበቀው ፀጋ ሲወጣ ከኮሮጆዬ መውደቁን አውቆ ፈርቶ ሸሽቶኛል ባለ ጋራዬ (2x) አዝ፦ አምላክ ያለው ይምጣ የእኔ አምላክ ልዩ ነው በምድረ በዳ ላይ ማኖር ልማዱ ነው (2x) እስቲ ልፎካከር በሰሜን በደቡብ በምስራቅ በምዕራብ እርሱ ነው እግዚአብሔር (2x) የተዘጋው ከፈተውና ከፊት ከፊቴ መሸነፍ ሳይሆን ያጋጥመኛል ድል በሕይወቴ (2x) የተዘራውን በቅሎ አየሁት አልጨነገፈም በድርቁ ወራት የሌላው ሲደርቅ የእኔ አልደረቀም (2x) አዝ፦ አምላክ ያለው ይምጣ የእኔ አምላክ ልዩ ነው በምድረ በዳ ላይ ማኖር ልማዱ ነው (2x) እስቲ ልፎካከር በሰሜን በደቡብ በምስራቅ በምዕራብ እርሱ ነው እግዚአብሔር (2x) ምን ልበል ምን ላድርግ ልቤ መደነቅ ተሞላ በአንዱ ስገረም ሌላው እዚህ ደግሞ ተዓምር ነው ከማለት ሌላ ድንቅ ነው ከማለት ሌላ ልዩ ነው ከማለት ሌላ (2x)