Song Lyrics

ሀሩሩ በረደ

Awtaru Kebede
Tenestoal
ሃሩሩ በረደ ጥላ በዝቶ ከጥሜም እረካሁ ውኃ ፈልቆ በቃ ሲል አበቃ መጨነቄ አሻገርከኝ ያንን ዘመን ጌታዬ አዝ፦ ያላለፍኩት ምን አለ በአንተ ጌታ ያልወጣሁት ምን አለ በአንተ ኢየሱስ ያልወረድኩት ምን አለ በአንተ ጌታ ያልተሻገርኩት ምን አለ በአንተ ኢየሱስ ተመሥገን በአንተ ሁሉን ችዬ አለፍኩት (4x) ሁልጊዜ ይነገር ስለ አንተ ነገር ስለ አንተ ዝና እስቲ ይወራ ያለፈ ይናገር ስለ አንተ ነገር ስለ አንተ ዝና እስቲ ይወራ አልተለየኸኝም በጭንቀቴ ደግፈህ አቆምከኝ መድኃኒቴ አጸናኸው እግሬን እንደ ዋላ እግር ከልቤ ልበልህ ተመሥገን አዝ፦ ያላለፍኩት ምን አለ በአንተ ጌታ ያልወጣሁት ምን አለ በአንተ ኢየሱስ ያልወረድኩት ምን አለ በአንተ ጌታ ያልተሻገርኩት ምን አለ በአንተ ኢየሱስ ተመሥገን በአንተ ሁሉን ችዬ አለፍኩት (4x) ሳስበው ወደ ኋላ ዞር ብዬ ከችግር የተነሳ ተጨንቄ ማን ያሳልፈኛል ያልኩትን አንተ እኮ ነህ ያሳለፍከኝ ጌታዬ አዝ፦ ያላለፍኩት ምን አለ በአንተ ጌታ ያልወጣሁት ምን አለ በአንተ ኢየሱስ ያልወረድኩት ምን አለ በአንተ ጌታ ያልተሻገርኩት ምን አለ በአንተ ኢየሱስ ተመሥገን በአንተ ሁሉን ችዬ አለፍኩት (4x) ሁልጊዜ ይነገር ስለ አንተ ነገር ስለ አንተ ዝና እስቲ ይወራ ያለፈ ይናገር ስለ አንተ ነገር ስለ አንተ ዝና እስቲ ይወራ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection