Song Lyrics

ደግሞ ቀኑ ሲጨልም

Awtaru Kebede
Tenestoal
ጠዋት ስነሳ ደስታ ይሆናል የትላንትናው ሃዘን ይርቃል እህል ባልበላም ፊትህ ያጠግበኛል ፀጋህ ከክፉ ይጋርደኛል ምህረትህ ከፊት ከኋላ ከቦኝ አቤት ይገርማል ስንቱን አለፍኩት አዝ፦ ደግሞ ቀኑ ሲጨልም ደግሞ ቀኑ ሲነጋ ደግሞ እርጥቡ ሲደርቅ ደግሞ ሁኔታ ሲርቅ አንዴ ወዶኛል (4x) ምን ያሰጋኛል አንዴ ወዶኛል (4x) ምን ያሰጋኛል አምላክ ሲረዳኝ አታዩም ዎይ ክረምቱ አልፎ በጋው ሲታይ ከዓለቱ ልውጣ ድምጼን ላሰማ ጌታ እንደ ረዳኝ ሰው ሁሉ ይስማ ያገለገልኩት ለሥሙ የለየኝ ቀን ቆጠረና ዋጋ ከፈለኝ አዝ፦ ደግሞ ቀኑ ሲጨልም ደግሞ ቀኑ ሲነጋ ደግሞ እርጥቡ ሲደርቅ ደግሞ ሁኔታ ሲርቅ አንዴ ወዶኛል (4x) ምን ያሰጋኛል አንዴ ወዶኛል (4x) ምን ያሰጋኛል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection