Song Lyrics

ኑሮዬን የታምራት

Awtaru Kebede
Lelitu Nega
በላይ በላዩ ላይ በረከት አዞልኛል አንዱን ሳልጨርሰው ሌላው ይከተለኛል ገና ሳልፈጽመው የጥያቄዬን ቃል መልሴ በደጅ ቆሞ በር ያንኳኳልኛል አዝ፦ ኑሮዬን የታምራት አድርጐታል (2x) የኔ እኮ ከሰው ሁሉ ለየት ይላል (2x) ትላንትናን አኑሬሃለሁ ዛሬን ደግሞ በታምራቴ ይልቅስ ተረጋግተህ ኑር ይለኛል ረድዔቴ ሂድ እንጂ ተረጋግተህ ኑር ይለኛል ረድዔቴ እረጋጋለሁ አንተ ካልክማ ልቤ ሰምቶሃል ቃልህን ጌታ (2x) ጭንቅ አይለዉም ልቤን ፍርሃት ፍርሃት ምን በወጣኝ ልፍራ ጌታ ሆኖኝ አባት የሰማዩ ወፎች ጠግበው ከአደሩ እንዴት እኔ አልኖርም እነሱ ከኖሩ አዝ፦ ኑሮዬን የታምራት አድርጐታል ኑሮዬን የምስጋና አድርጐታል የኔ እኮ ከሰው ሁሉ ለየት ይላል (2x) ትላንትናን አኑሬሃለሁ ዛሬን ደግሞ በታምራቴ ይልቅስ ተረጋግተህ ኑር ይለኛል ረድዔቴ ሂድ እንጂ ተረጋግተህ ኑር ይለኛል ረድዔቴ እረጋጋለሁ አንተ ካልክማ ልቤ ሰምቶሃል ቃልህን ጌታ (2x) ስለለመድኩኝ ነው የታምራት ኑሮ ቀርቷል አትበሉኝ ተዓምርማ ድሮ ተዓምር የፈለገ ወደዚህ ይመልከት ዝንድሮም ይሰራል ጌታ በኛ ሕይወት አዝ፦ ኑሮዬን የታምራት አድርጐታል (2x) የኔ እኮ ከሰው ሁሉ ለየት ይላል (2x) ትላንትናን አኑሬሃለሁ ዛሬን ደግሞ በታምራቴ ይልቅስ ተረጋግተህ ኑር ይለኛል ረድዔቴ ሂድ እንጂ ተረጋግተህ ኑር ይለኛል ረድዔቴ እረጋጋለሁ አንተ ካልክማ ልቤ ሰምቶሃል ቃልህን ጌታ (2x) እንደዘመርኩት ነው ኑሮዬ መሠረቴ ሆኗል ጌታዬ ወጀቡ ቢበዛ ቢያይልም ቢገፋኝ የሚገፋኝ አልወድቅም (4x) እረጋጋለሁ አንተ ካልክማ ልቤ ሰምቶሃል ቃልህን ጌታ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection