ማልጄ ደግሞ ስነሳ ስለውለታህ ላነሳሳ ሌቱም አልበቃ አልበቃ አለኝ ቀኑም እጥር እጥር አለብኝ የተደረገልኝ ራሴው ነው የማውቀው ዛሬ እዚህ መድረሴ ጌታዬ በአንተ ነው ሳስበው የትላንቱን (አሃሃ) አስጨናቂ መንገዱን (ኦሆሆ) በፀጋህ ደገፍከኝና (አሃሃ) ገረመኝ አለፍኩትና (2x) በአንተ ነው የእኔ ጌታ (4x) እረካሁ ከእጅህ ጠጥቼ (አሃሃ) ወጣሁት ጉልበት አግኝቼ (አሃሃ) አልቀረሁ በምድረ በዳ (አሃሃ) አትወድም ሰው እንዲጐዳ (አሃሃ) (2x) በአንተ ነው የእኔ ጌታ (4x) አንተ ለእኔ ለእኔ የምታስበው መልካም ነዉ ጌታ ለእኔ የምታስበው መልካም ነዉ ቆጥሬው ተናግሬው (አሃሃ) ከውስጤ የማይወጣው (አሃሃ) ጌትዬ ለእኔ ያደረገው (አሃሃ) ከቁጥር ያለፈ ነው (አሃሃ) (2x) በአንተ ነው የእኔ ጌታ (4x)