የልብ ልቤን ላውጣው እስቲ ልናገር ጌታ ያደረገልኝ አለኝ ብዙ የሚነገር እርሱ ያደረገልኝ አለኝ ስሙኝ የሚነገር (2x) የእኔ ወዳጅ ነህ የእኔ የራሴ መተኪያ የሌለህ ኢየሱሴ ከስንቱ ቦታ ስንቱን አሻግረህ ሊዚህ ያደረስከኝ አንተ እኮ ነህ (2x) ፀሐዩ ሲጠልቅ ጨለማው ሲመጣ ንጉሥ ንጉሥን ሽሮ አንዱ በአንዱ ፈንታ ለሁሉም ጊዜ አለው ጉልበቱ ሊፈታ የማትለዋወጥ የማትቀያየር አንተ ብቻ ጌታ(2x) አለኸኝ የምለው የእኔው ነህ የምለዉ አንተኑ አንተኑ ነዉ አንተኑ አንተኑ ነዉ (2x) የልብ ልቤን ላውጣው እስቲ ልናገር ጌታ ያደረገልኝ አለኝ ብዙ የሚነገር እርሱ ያደረገልኝ አለኝ ስሙኝ የሚነገር (2x) የእኔ ወዳጅ ነህ የእኔ የራሴ መተኪያ የሌለህ ኢየሱሴ ከስንቱ ቦታ ስንቱን አሻግረህ ሊዚህ ያደረስከኝ አንተ እኮ ነህ (2x) ወንዝ አያሻግርም የቅርብ ወዳጅ ሆኖ ፍቅር ዛሬ የለም ይላል ቀረ ድሮ ሁኔታ ሲለወጥ ከአለበት ቦታ የማትለዋወጥ የማትቀያየር አንተ ብቻ ጌታ( አለኸኝ የምለው የእኔው ነህ የምለዉ አንተኑ አንተኑ ነዉ አንተኑ አንተኑ ነዉ (2x) አንተኑ አንተኑ ነዉ (3x)