Song Lyrics

በሕይወት አለሁ

Awtaru Kebede
Lelitu Nega
ተወራረድኩበት በዚህ ታማኝ ጌታ አይጥለኝም አልኩኝ እኔንም ለአንድ አፍታ (ኦሆ ለአንድ አፍታ) የድሮ ቃልኪዳን በልቤ ውስጥ ገብቶ ፎከርኩኝ በአምላኬ አይተወኝም ከቶ (ኦሆ እኔን ከቶ) እንደ ዓይኑ እኔን ሲያይ ገረመኝ ጌታ ከላይ ምህረቱ ገንኖ ነው ለካ ያለፍኩት ያንን ጨለማ (2x) ዞር ዞር አልኩና ወደ ግራ ወደ ቀኝ (ወደ ግራ ወደ ቀኝ) ከፊትም ከኋላም ሲጠፋ የሚረዳኝ (ሲጠፋ የሚረዳኝ) ዓይኖቼን ሳነሳ ወደ የዋሁ ጌታ (ወደ ጀግናው ጌታ) ችግሬን አጣሁት እሱን ባየሁ ለታ (እሱን ባየሁ ለታ) ጌታ እንደሌለው እንደሌለው እንደማንም እኔስ አይደለሁም ቀና ስል ወደ ላይ ወደ አምላኬ ልመናዬን ሰማኝ ተንበርክኬ (2x) በቅጡ አውቀዋለሁ የኔን ጌታ ያሻግራል ቃሉማ መልካም ቦታ ሰንቆም ላከልኝ መልሴን ፈጥኖ ያንን ክፉ ዘመን በቃ ብሎ (2x) ምንድነው ሚሰማው በከተማው ወሬ ሞቷል አትበሉ በሕይወት አለሁ ዛሬ (ኦሆ አለሁ ዛሬ) እንደ እግዚአብሔር ሃሳብ ወደ ግብጽ ቢወርድም ህልሙ ሳይፈጸም ባለራዕይ አይሞትም (በፍጹም አይሞትም) እንደ ዓይኑ እኔን ሲያይ ገረመኝ ጌታ ከላይ ምህረቱ ገንኖ ነው ለካ ያለፍኩት ያንን ጨለማ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection