Song Lyrics

ሌሊቱ ነጋ

Awtaru Kebede
Lelitu Nega
እስከዛሬ ከአንተ ጋር ኖሬ ተጉዤያለሁ ብዙ አብሬ አንዱ ሲሄድ አንዱ ሲመጣ አትለወጥ አንተ ግን ጌታ ጥቁር አይል ፊትህ አይቀየር አትዘጋም የምህረትን በር ኧረ ስንቱ ጭንቁን እረስቶ እፎይ ብሏል አንተ ላይ ታምኖ (2x) ያው ነህ (8x) አልወደቅኩም በፈራሁት ላይ የእኔ ኢየሱስ ዓይን ዓይኖቼን ሲያይ ከእናት ከአባት ከወዳጅ ይልቅ ጠብቆኛል ክፉ ላይ እንዳልወድቅ ዞር አረገው ከፊቴ ቀድሞ ያንን ሃዘን ለእኔ አስቦ የተማሰው ጉድጓድ ተዘጋ በአንድ አፍታ ለሊቱ ነጋ (2x) ያው ነህ (8x) ብርድ አለ የሃሩሩ ጊዜ እንደ ህልም አለፈ የሃዘን ትካዜ (2x) ትንግርት ነው የፍቅር ጉልበት ለወደቀው የደረሰለት የአለበት ጓዳ ውስጥ ገብቶ አቁሞታል ዘይት ቀብቶ ሰው የለኝም በግራ በቀኝ ጉልበት ጠፋ አቅም አጣሁኝ ብሎ ለሚል ፍቅር አለው መላ ታሪክ ከፍቶ ያሳያል ሌላ የእኔ ወዳጅ ነህ የእኔ (የእኔ) የእኔ አባት ነህ የእኔ (የእኔ) የእኔ እረኛ ነህ የእኔ (ኦኦኦ) የእኔ ጋሻ ነህ የእኔ (2x) የእኔ ወዳጅ ነህ የእኔ (የእኔ) የእኔ አባት ነህ የእኔ (የእኔ) የእኔ ፍቅር ነህ የእኔ (ኦኦኦ) የእኔ እረኛ ነህ የእኔ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection