አምልኬ አልጠግብ አልኩ ጌታዬ አንግሼ አልጠግብ አልኩ ወዳጄ አጣሁ አጣሁኝ አንተን የሚተካ በምድር በሰማይ አንደኛ ነህ ለካ (2x) ምነው ሌላ ቋንቋ ሌላ ሌላ ቋንቋ ቢኖረኝ/ቢፈጠር ልብን የሚያረካ (2x) አልወጣልህ አለኝ ከልቤ እስቲ ላመስግንህ ጌታዬ ጌታዬ አዝ፦ ያለኝ ይሄ ነው ያለኝ (4x) አጣሁልህ ኢየሱስ አንተን መሳይ የከበረ በምድር በሰማይ ፍቅርህ ልቤን ጥብቅ አድርጐ ይዞታል እስቲ ዘምር አመስግን ያሰኘናል ሥምህ የከበረ የገነነ ነዉ ነዉ ዝናህ የከበረ የገነነ ነዉ ነዉ ጌታ ነህ ጌታ ነህ ከሁሉ በላይ እንዳንተ ያለ በምድር የለም በሰማይ (2x) ሰው ያለኝ ይሄ ነው እያለ ሲያወራ የእኔ ግን ጌታ ነው የለውም እኩያ (2x) አዝ፦ ያለኝ ጌታ ነው ያለኝ (2x) ያለኝ እርሱ ነው ያለኝ (2x) አምልኬ አልጠግብ አልኩ ጌታዬ አንግሼ አልጠግብህም አልኩ ወዳጄ አጣሁ አጣሁኝ አንተን የሚተካ በምድር በሰማይ አንደኛ ነህ ለካ (2x) ምነው ሌላ ቋንቋ ሌላ ሌላ ቋንቋ ቢኖረኝ/ቢፈጠር ልብን የሚያረካ (2x) አልወጣልህ አለኝ ከልቤ ውለታህ በዛብኝ ጌታዬ ጌታዬ አልወጣልህ አለኝ ከልቤ እስቲ ላመስግንህ ጌታዬ ጌታዬ አዝ፦ አዝ፦ ያለኝ ይሄ ነው ያለኝ (4x)