Song Lyrics

ኢትዮጵያን አስብልን

Ethiopian Asibilin

Aster Abebe
Special Edition
አቤቱ ፀሎታቸን መልስልን ኢትዮጵያን አስብልን ጌታ ሆይ እንባችንን አብስልን ምድራችንን ጎብኝልን ምህረትህ ይብዛ ማረን እንላለን እጆቻችንን ወዳንተ ዘርግተን ከክፉ መንገድ እንመለሳለን ከእግርህ ስር ወድቀን እንጮሀለን በእውነት ፊትህን ፈልገን መጥተናል ይቅር በለን የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ ተነስ ተነስ ተነስ ዘንዶውን የወጋህ አንተ አይደለህ ረአብን የቆራረጥክ አንተ አይደለህም ወይ (4X) ተነስ ተነስ እጅህም ይዘርጋ ፊትህን መልስ እንደቀድሞው ሀይልን ልበስ ተነስ ተነስ እጅህም ይዘርጋ ፊትህን መልስ ዛሬም ና ተንቀሳቀስ አቤቱ ፀሎታችን መልስልን ኢትዮጵያን አስብልን ጌታ ሆእ እንባችንን አብስልን ምድራችንን ጎብኝልን ጨለማው አልቆ ለቆ ሁሉን ስፍራ የወንጌል ብርሀን በምድሪቱ ይብራ ጉስቁልናችን ቀርቶልን አበሳ ሰላምና ፈውስ እረፍት ይሁን ይብዛ በረከትንም አፍስሰህ አሳየን አትረፍርፈህ የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ ተነስ ተነስ ተነስ ዘንዶውን የወጋህ አንተ አይደለህ ረአብን የቆራረጥክ አንተ አይደለህም ወይ (4X) ተነስ ተነስ እጅህም ይዘርጋ ፊትህን መልስ እንደቀድሞው ሀይልን ልበስ ተነስ ተነስ እጅህም ይዘርጋ ፊትህን መልስ ዛሬም ና ተንቀሳቀስ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection