Song Lyrics

ትልቅ የሆነውን

Aster Abebe
Kibir Yebekah Neh
ትልቅ የሆነውን ከፊቴ አስቀድሜ መቼ አንገቴን ደፋሁ መች ሄድኩ አቀርቅሬ የተማመንኩበት ኩራቴ ሆኖኛል ትላንቴ ይመስክር ሰልፌን አሸንፏል ሰልፌን አሸንፏል ( 2x) ከፍታውን ተመኝቶ ከፍ ብያለሁ ያለ ላፍታ ማን ተመቸው ማን ተደላደለ ወርዷል ወደ ቦታው እርሱ ወዳዘዘለት ልክን ማወቅ እያለ ኋላ ከመዋረድ በዕውቀቱ ልቀት ማንስ ገለጠው እንኳንስ የእርሱን ጥግ ጫፉን ማን ነካው ሁሉም ከታች ሆኖ ይመለከተዋል የእጁ ስራ ሁሉ ሲያደንቀው ይኖራል ከቶ አልደፍርም አንደኛ ልለው ሁለተኛ ሆኖ ማን ተከተለው ሁሌ ብቻውን ሚመለክ ትልቅ ሚጨምር ክብር ከትላንቱ ይልቅ ( 2x) ደጋግሞ ቢፎክር ቢጨምር ቀረርቶ ልቡን አጥፍቶታል ከሰማያት ወርዶ ዝቅ ብሎ ያለ ልክ ታዞ በመስቀል ላይ የአብን ጥም አርክቷል ሆኗል የአለም ሲሳይ ግድግዳው ፈረሰ በመሀከል ያለው ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ለይቶ ያቆየው ፍቅር መሀል ገብቶ ሁሉን አንድ አረገ ጠላትም አፈረ ለወልድ እጁን ሰጠ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection