Song Lyrics

ይሆንልኛል

Aster Abebe
Kibir Yebekah Neh
ይሆንልኛል ይሳካልኛል ሥጋት ሰፈሬን ከራቀ ሰንበትበት ብሏል (፬x) አልረሳውም ማንነቴን በደም ዋጋ መገዛቴን ንጉሥ ከላይ ሆኖ እንዳየኝ ልጄ ምርጤ ርስቴ እንዳለኝ ( 2x) በምሰማው ሌላ ውሸት አልጥለውም ይህን ዕውነት ንጉሥ ልጁን የላከልኝ የተወደድኩ ምርጥ ዘር ነኝ ( 2x) አይሆንም አይሰምርም ያለው ኧረ ማን ነው? ሁኔታ ነው? ነቅቻለሁ! ቃሉን በንጉሥ ቃል ሽራለሁ ተደርጐልኛል ተሳክቶልኛል ይህን አውቃለሁ አይሆንም አይሰምርም ያለው ኧረ ማን ነው? ጠላቴ ነው? ነቅቻለሁ! ቃሉን በንጉሥ ቃል ሽራለሁ ይሆንልኛል ይሳካልኛል ይህን አውቃለሁ ቁም ነገር አድርጐት የእኔን ጉዳይ ክብሩን ሁሉ ትቶ ወርዷል ከላይ አቅሜን አውቃለሁ በእርሱ ያለኝን የሆንኩትን ሆኖ ያረገኝን ( 2x) ደዌ በእኔ ላይ ላይሰለጥንእርግማን በቤቴ እንዳይገኝ ዝቅታ ላይሆንብኝ በላዬመሸነፍ መረታት ላያገኘኝ ከፍ ላለ ሕይወት በክርስቶስ ታጭቻለሁ ይህ ነው ዕጣ ፈንታዬ የሆንኩትን ሁሉ ሆኖልኛል በድል ተፈጽሟል ጐዳናዬ ያለቀ ነው ያኔ ድሮ የእኔ ጉዳይ የእኔ ኑሮ በቀራኒዮ ተራራ ላይ ተፈጽሟል ብሎኛል የእኔ ጉዳይ ( 2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection