Song Lyrics

መንፈስ ቅዱስ

Aster Abebe
Kibir Yebekah Neh
አለህ በውስጤ ሰላምህ በዝቶልኛል አለህ በላዬ ድል ማድረግ ሆኖልኛል አለህ ከጎኔ ስትረዳኝ አየሁህ አለህ በቤቴ ህይወቴን አጣፈጥህ ( 2x) አዝ፦ መንፈስ ቅዱሰ መጽናኛዬ አቅሜ ነህ ጉልበት ሃይሌ አማላጄ ነህ ደጀኔ አቅም ሀይሌ ጓደኛዬ አንድ የሆነ ጉዳይ ከእኔ ጋር እስክትጨርስ ድረስ አይደለም ለጊዜ ወደ አብ እስከምትመለስ ሁሌም ክእኔ ጋር ነህ ሆነሃል ወዳጄ በውስጤ በላዬ ከጎኔ ከደጄ ( 2x) አዝ፦ መንፈስ ቅዱሰ መጽናኛዬ አቅሜ ነህ ጉልበት ሃይሌ አማላጄ ነህ ደጀኔ መበርቻዬ ጓደኛዬ እውርነት ቀርቶ ማየት ጀምሬያለሁ የልቦናዬን አይኖች በአንተን አግኝቻለሁ ድፍርሱን ህይወቴን በምክርህ አጥርተሃል ያላንተ እንደማልኖር ልቤ ይህን አውቋል ( 2x) አዝ፦ መንፈስ ቅዱሰ መበርቻዬ አቅሜ ነህ ጉልበት ሃይሌ አማላጄ ነህ ደጀኔ አቅሜ ኃይሌ ጓደኛዬ መጽናኛዬ ጓደኛዬ አለኝታዬ ጓደኛዬ መበርቻዬ መጽናኛዬ አለኝታዬ ጓደኛዬ መኖር ኣልችልም ያላንተ ፈራለው ሁሉም ዝግትግት ያለ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection