Song Lyrics

ክብር የበቃህ ነህ

Aster Abebe
Kibir Yebekah Neh
አዝ፦ ቀድሞም ክብር የበቃህ ነህ ሞልቶ የተረፈህ ተገብቶህ እንጂ ማን ሰጥቶህ ያውቃል ስለጎደለህ አንሶብህ ምሥጋናና ክብር አደባባይ ወጥተህ ማትለምን ኢየሱሴ ትልቅ ነህ ምትደነቅ ( 2x) ቀን አንድ ተብሎ ሳይጀመር አንተኮ ስትመለክ ነበር ወር አንድ ተብሎ ሳይቆጠር አንተኮ ስትመለክ ነበር ዓመት በዓመት ላይ ሳይደመር አንተኮ ስትመለክ ነበር በዘመናት ዘመን ሳይጨመር አንተኮ ስትመለክ ነበር ሳይባል በመጀመሪያ ሳትፈጥር ሰማይና ምድርን አዕዋፋት ባየር ላይ ሳይበሩ ሳትመሰርት በፊት ተራሮችን ገና ሳታበጅ ሰውን በጅህ ሳይወጣ እስትንፋስ ከአፍህ ሁሉ ነገር ምንም ባዶ እያለ ምሥጋናህ ግን ሞልቶ የተረፈ አዝ፦ ቀድሞም ክብር የበቃህ ነህ ሞልቶ የተረፈህ ተገብቶህ እንጂ ማን ሰጥቶህ ያውቃል ስለጎደለህ አንሶብህ ምሥጋናና ክብር አደባባይ ወጥተህ ማትለምን ኢየሱሴ ትልቅ ነህ ምትደነቅ ( 2x) ቀን አንድ ተብሎ ሳይጀመር አንተኮ ስትመለክ ነበር ወር አንድ ተብሎ ሳይቆጠር አንተኮ ስትመለክ ነበር ዓመት በዓመት ላይ ሳይደመር አንተኮ ስትመለክ ነበር በዘመናት ዘመን ሳይጨመር አንተኮ ስትመለክ ነበር ሳይባል በመጀመሪያ ሳትፈጥር ሰማይና ምድርን አዕዋፋት ባየር ላይ ሳይበሩ ሳትመሰርት በፊት ተራሮችን ገና ሳታበጅ ሰውን በጅህ ሳይወጣ እስትንፋስ ከአፍህ ሁሉ ነገር ምንም ባዶ እያለ ምሥጋናህ ግን ሞልቶ የተረፈ ቀድሞም ክብር የበቃህ ነህ ሞልቶ የተረፈህ ተገብቶህ እንጂ ማን ሰጥቶህ ያውቃል ስለጎደለህ አንሶብህ ምሥጋናና ክብር አደባባይ ወጥተህ ማትለምን ኢየሱሴ ትልቅ ነህ ምትደነቅ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection