የመራቄ ርቀት ከኣብ መለያየቴ ማን ግድ ብሎት ነበር የመንከራተቴ ክብሩ በጎደለው ህይወት ስመላለስ ርቄ ከፈቃዱ መታደሴ እስኪደርስ ከመላዕክት መካከል ወይም ከሰማዕታት ቀድመው ከነበሩት ከተባሉት አባት ማን በጥቂት ጣረ ወደ አብ ሊያስጠጋኝ ህጉስ ምን ፈየደኝ ይብሱን አጣላኝ አብ አባት ራርቶልኝ ሊታረቀኝ ወዶ በእቅፉ ያለውን አንድ ልጁን ልኮ ሃጥያት የማያውቀውን ሃጥያት አደረገው ከድምፁ ያራቀኝን የዕዳ ጽህፈቴን በደሙ ገሰሰው ማነው ያለው ተገዳ ነው? የራሱ ያደረገኝ መውደዱ ማርኮኝ ነው ማነው ያለው ቸግሯት ነው? ርስቱ ያደረገኝ ፍቅሩ ገዝቶኝ ነው መች አጠረች እጁ ከማዳን መች ተሳናት ጆሮው ልትሰማን እውነት ስፍራን አጥቶ ጽድቅ ርቆ ቆሞ ህያው ነፍስ በሙሉ ለሃጥያት ታድሞ ማላጅ እንደሌለ ምድርን አየች አይኑ ጽድቁም አገዘችው ፈጠነች ማዳኑ በገዛ ክንዶቹ መድሃኒት ሆነልን ፍጥረቱ ታደሰ በስላሴ ምክር