በእረኝነቱ ተመርቻለሁ ጠንቀቅ አድርጌም ድምፁን አውቃለሁ በአረንጓዴው መስክ ባማረው ላይ አንሰራፍቶኛል ሳይኖር ከልካይ አልፈራም አውሬ ደፋር አርጎኛል የአራዊት ድምፅ መቼ ያስፈራኛል ባለመናወጥ ከምንጩ ልርካ ከጭንቀት ማረፍ እንዲህ ነው ለካ እንዲህ ነው ለካ አሃ እንዲህ ነው ለካ (፬x) ኧረ እንዴት ተለዪው ይሉኛል ይህን የቅርብ ወዳጄን ኧረ እንዴት ተለዪው ይሉኛል ይህን የበረሃ ጓዴን ኧረ እንዴት ተለዪው ይሉኛል ይህን ሚስጢረኛዬን ኧረ እንዴት ተለዪው ይሉኛል ይህን መልካም እረኛዬን አልለየውም አልለየውም ያለ እርሱ መኖር እኔስ አልችልም አልለየውም አልለየውም ያለ እርሱ ውበት ወዝም የለኝም ( 2x) ዝቅ ዝቅ ያልኩትን ያለ ከፍታዬ ከፍ ከፍ ያረገኝ ወገን ያልሆንኩትን በልጁ ልጅ አርጎ ማዕረግን ያሳየኝ የተደረገውን በጎነት ቸርነት አልችልም መሸከም የምልህ የለኝም በሰጠኸኝ ዘመን ከፊት ፊቴ ቅደም ብርታቴ እኮ ነህ ብርታቴ ህይወቴ እኮ ነህ ህይወቴ ጉልበቴ እኮ ነህ ጉልበቴ ኢየሱስ ለእኔ መድኃኒቴ ( 2x) መድኃኒቴ መድኃኒቴ ( 2x)