Song Lyrics

ኃያል አደረከኝ

Aster Abebe
Kibir Yebekah Neh
ሥምህን አውቅኩት ተረዳሁት ደግሞም ታምኜበታለሁ የፀና ግንብ ነው ከስንቱ አምልጬ ተጠግቼው ከፍ ከፍ ብያለሁ ደጅህን ጠናሁት አንኳኳሁት ከፍተህልኝ ተቀብለኸኛል በፍቅር እጆችህ እቅፍ አርገህ ወደ ራስህ አስጠግተኸኛል ( 2x) አቤት ያለው ሰላም ከአንተ ጋር ሲጠጋጉ ወደ ደረትህ ማዳመጥ ስትናገር የፍቅርን ቋንቋ መቼ ይታወቃል ወፎቹ ሲንጫጬ ለሊቱም ሲነጋ ( 2x) ኃያል ሆይ በኃይልህ ኃያል አደረግከኝ ብርቱ ሆይ በብርታትህ ብርቱውን አደረግከኝu እየማርክኝ እየማርክኝ እየማርክኝ እየማርክኝ እየማርክኝ እየማርክኝ እየማርክኝ እየማርክኝ ( 2x) በልዑሉ አምላክ መጠጊያ መኖሬ ሁሉን በሚችለው ጥላ ውስጥ ማደሬ ይሄ ካላስመካኝ የቱ ያስመካኛል መታመኛዬ ነው ከእልፍ አስጥሎኛል ከክንፎቹ በታች በላባዎቹ ጋርዶኝ ከጠላት ፍላፃ አንዱም አላገኘኝ ይሄ ካላስመካኝ የቱ ያስመካኛል መታመኛዬ ነው ከእልፍ አስጥሎኛል በአጠገቤ ሺህ በቀኜም አስር ሺህ እየበተነልኝ ሆኛለሁ ድል ነሺ ይሄ ካላስመካኝ የቱ ያስመካኛል መታመኛዬ ነው ከእልፍ አስጥሎኛል አስጥሎኛል እንዲህ አድርጎ ከአንደበቴ ምስጋናን ወዶ (፰x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection