አይኖቼን የከፈትህ ከጽድቅህም ቃል ያስተማረከኝ፤ የተሻለውን ምርጫ እንድመርጥ ማስተዋልን የሰጠኸኝ፤ አንተ አምላኬ እንደሆንህ በማወቄም እረፍት ሆነልኝ፤ ላመስግንህ እጄን ላንሳ በእድሜዬ ስላደረክልኝ። 2× ህግህ ፍጹም ነው ነፍሴን አለምልሟታል፤ ስርዓትህ የታመነ ነው ጥበበኛም አድርጎኛል፤ የአፍህ ቃል ትክክል ነው ልቤን ደስ አሰኘው፤ ትዕዛዝህ ብሩህ ነው አይኔን ለእውነት ከፈተው። (ዓለም ሳይፈጠር የመረጥከኝ፤ ጊዜው ሲደርስ በአንድ ልጅህ ልጅህ ያደረከኝ፤)2× በርህራሄ ገመድ በፍቅርህ ሰንሰለት፤ (ስበህ የራስህ ያደረከኝ፤ አብ አባት ነህ ዓለም ሁሉ ይወቅልኝ።) 2× እንደምትመግብ ንስር ጫጩቶቿን፤ እንደምትሰበስብ ዘርግታ ክንፎቿን፤ እንደምታሳድግ ከልክላ ከክፉ፤ የአቅመቢስ ቀናቸውን ዘልቀው እስኪያልፉ፤ (ለእኔም አንተ እንዲሁ አይደለህም ወይ? ማምለጫ ዋሻዬ ክፉውን ቀን ከልካይ፤ እንደማንነትህ ሳይሆን ዝቅ ብለህ ያጎረስከኝ፤ የእድሜልክ መምህሬ "ሀ" ብለህ ያስቆጠርከኝ።) 2× ገመድህ ርህራሄ ነፍሴን ያሰርክበት፤ ሰንሰለት ነው ፍቅርህ ከእግርህ ያዋልክበት፤ (አፍ ያልፈታው ፍቅሬ አንድ ሊል ጀመረ፤ በጉልበት አይደለም ከፍቅርህ ተማረ።) 2× (ዓለም ሳይፈጠር የመረጥከኝ፤ ጊዜው ሲደርስ በአንድ ልጅህ ልጅህ ያደረከኝ፤) 2× በርህራሄ ገመድ በፍቅርህ ሰንሰለት፤ (ስበህ የራስህ ያደረከኝ፤ አብ አባት ነህ ዓለም ሁሉ ይወቅልኝ።) 2× በባሕር አስጥመህ ተበቀልክ ጠላትን፤ ውኃን እያፈለቅክ ሰንጥቀህ አለቱን፤ መናን እያዘነብክ በየማለዳው፤ የማዳንህ መንገድ ህዝብህ መች ገባው፤ (በማህጸን አደረ እንደ ሰው ወግ ልማድ፤ ላከው ወደ ምድር ቆጥሮ ዘጠኝ ወራት፤ ካልጠፋ ውብ ቦታ ካልታጣ ንጹህ ቤት፤ መረጥክለት ግርግም የከብቶችን በረት።) 2× ተራራ ልብ ያለው ዝቅ ብሎ ስሞታል፤ ስንቱ ጠቢብ ነኝ ባይ ከእግሮቹ ስር ሰግዷል፤7 (እረኞችም ነኩት አልናቃቸው ፍቅርህ፤ ሁሉን ያሰርክበት ልጅህ ነው ገመድህ።) 2× (ዓለም ሳይፈጠር የመረጥከኝ፤ ጊዜው ሲደርስ በአንድ ልጅህ ልጅህ ያደረከኝ፤) 2× በርህራሄ ገመድ በፍቅርህ ሰንሰለት፤ (ስበህ የራስህ ያደረከኝ፤ አብ አባት ነህ ዓለም ሁሉ ይወቅልኝ።) 2×